አጋራ

የጡት ካንሰር በጡት ውስጥ የሚጀምር የካንሰር አይነት ነው። በአንድ ወይም በሁለቱም ጡቶች ውስጥ ሊጀምር ይችላል:: የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች አንዱ ሲሆን፣ ነገር ግን <1% ባነሱ ወንዶችም ላይ ጡት ካንሰር ሊከሰት ይችላል። 

ሴቶች ምንም አይነት ያልተለመዱ ነገሮችን ለመፈተሽ በየጊዜው የራስ ጡት ምርመራ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። የወር አበባ እያየች ላለች ሴት በየወሩ ከቆመ ትንሽ ቀን በኋላ የራስ ጡት ምርመራ ማረግ ይመረጣል። ማረጥ ላይ ለደረሱ ሴቶች ግን በየወሩ በተመሳሳይ ቀን የራስ ጡት ምርመራ ማረግ ዪመረጣል።

 ገና የወር አበባ ላይ ላሉት ሴቶች ጡትን እራስ መመርመር ያለባቸው የወር አበባዋ ካለቀ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲሆን ማረጥ ላይ ለደረሱ ሴቶች ደሞ በየወሩ በተመሳሳይ ቀን መደረግ አለበት።

ሻወር ውስጥ 

ሶስቱ መሃከለኛ ጣቶችዎ ጠፍጣፋ በማረግ መላውን የጡት እና የብብት አካባቢ ብርሃን ባለበት ቦታ ጫን ጫን ያርጉ። በየወሩ ሁለቱንም ጡቶች ይፈትሹ። አዲስ እብጠት እና የጡት ለውጦች ያስተውሉ። 

በመስታወት ፊት 

ክንዶችዎን ከጎንዎ በማድረግ ጡቶቻችሁን በእይታ ይመርምሩ። በጡቶች ቅርጽ ላይ ያሉ ለውጦችን፣ ማበጥ ወይም የቆዳ ችግሮች እና በጡት ጫፍ ላይ ያሉ ለውጦችን ይፈልጉ።

በመቀጠል እጅዎትን ከፍ ማድረግ ወይም መዳፍዎን በወገብዎ ላይ ያሳርፉ እና የደረትዎን ጡንቻዎች ያጠንክሩ። ማናውንም ለውጦችን ይፈልጉ። የግራ እና የቀኝ ጡቶች ግን በተፈጥሮ በትክክል እንደማይዛመዱ ልብ ይበሉ! የጥቂት ሴቶች ጡቶች ብቻ ነው ፍጹም እኩል የሚሆኑት።

በመተኛት

በሚተኛበት ጊዜ ጡቱ በደረት ላይ በደንብ ይሰራጫል። ትራስ በቀኝ ትከሻዎ ስር ያስቀምጡ እና ቀኝ ክንድዎን ከጭንቅላቱ ጀርባ ያድርጉት። በግራ እጃችሁ በመጠቀም የ 3 ቱን መሃከለኛ ጣቶችዎን በቀኝ ጡትዎ ዙሪያ ያንቀሳቅሱ። የጡት አካባቢ እና ብብት በደንብ ያካልሉ።

አዲስ እብጠቶች፣ ውፍረቶች፣ የደነደነ ቋጠሮዎች ወይም ሌሎች የጡት ለውጦች ለመለየት ቀላል፣ መካከለኛ እና ጠንካራ የጣት ግፊት ይጠቀሙ። እንዲሁም ፈሳሽ መውጣቱን ለመፈተሽ የጡት ጫፉን ይጭመቁ። እነዚህን እርምጃዎች ለግራ ጡትዎ ይድገሙ።

እንደነዚህ ያሉትን ምልክቶች ልብ ይበሉ፦

  • ከጡትማጥባት ውጭ የጡት ፈሳሽ ወይም ጫፍ ማመም
  • የጡቱ የቆዳ ሸካራነት፤ ቀይ መሆን ወይም ማበጥ (ከብርቱካን ልጣጭ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የቆዳ ለውጥ)
  • በጡት ውስጥ ያለ እብጠት ወይም በጡት እና በክንድ አካባቢ ያለ እብጠት 

ምርመራ በሚያደርጉበት ጊዜ ከተጠቀሱት ምልክቶች አንዱን ካገኙ እባክዎን ለምርመራ ዶክተርዎን ይጎብኙ። ሁሉም እብጠቶች ነቀርሳ (cancer) አይደሉም። ነገር ግን ሁሉም እብጠቶች በጤና ባለሙያ መመርመር አለባቸው።