አጋራ

ለወጣት ሴት ልጅ የመጀመሪያ የወር አበባዋ ለማየት በጣም የተለመደው እድሜ 12 ነው። ነገር ግን የመጀመሪያ የወር አበባ ሲመጣ ልጃገረዶች ከ8 እስከ 16 ዓመት ሊሆናቸው ይችላል። ሁለቱም በሴት ልጅ ላይ የራሳቸው አካላዊ እና አእምሮአዊ ተፅእኖ አላቸው። ምንም ቢሆን ግን ለእያንዳንዱ ልጃገረድ የተለየ እና የራሱ የሆነ ጊዜ ቢኖችርም ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣ የወር አበባ ጊዜያት የተለያዩ ምክንያቶች አሉት።. ደግነቱ ሴት ልጅ የወር አበባዋን የምታገኝበትን ቀን ለመተንበይ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የስነ ተዋልዶ ጤናን ለመመስረት አንዳንድ ማሻሻያዎችን እንድታደርግ የሚረዱት ጥቂት መንገዶችም አሉ።

ብዙውን ጊዜ የመጀመሪያው የወር አበባ የሚከሰተው የመጀመሪያዎቹ የጉርምስና ምልክቶች ከታዩ ከ 2 ዓመት በኋላ ነው። በውጤቱም የወር አበባዋ ሊመጣ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳንድ ምልክቶች (የጉርምስና መደበኛ ባህሪያት እንደ ጡት እድገት፣ ዳሌ መጨመር እና የመሳሰሉት ናቸው። ሌሎች ምልክቶች እንደ የእድገት መጨመር፣ የማህፀን ፈሳሾች፣, ቁርጠት እና የጡት "እብጠቶች" ናቸው. የመጀመሪያው የወር አበባ እድሜ የሚወሰነው በጂኖች (genes), በሆርሞኖች, (BMI) እና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በጤንነት ነው።

ከጊዜ ቀድሞ የወር አበባ መጀመር ምክኒያቶች

የመጀመሪያ ወር አበባ በ10 አመት ሲጀምር ከጊዜ ቀድሞ የጀመረ የወር አበባ ይባላል

ጄኔቲክ ምክንያቶች

ክፍ ያለ ዉፍረት ክቁመት አንጻር

ያለ አግባብ ከእድሜ በጣም ቀድመው የጉርምስና ምልክቶች ሲመጡ

ጣፋጭ ነገር በብዛት መመገብ

የተለያዩ የጤና ችግሮች

አካል ብቃት እንቅስቃሴ የሌለበት ኑሮ

ከጊዜ አልፎ የወር አበባ መጀመር ምክኒያቶች

የመጀመሪያ ወር አበባ ከ15 አመት በኋላ ሲጀምር ከጊዜ አልፎ የጀመረ የወር አበባ ይባላል።

ጄኔቲክ ምክንያቶች

በእንቅርት ውስጥ የሚመረቱ ንጥረ ነገሮች ሲያንሱ

ፒቱታሪ ውስጥ የሚመረቱ ንጥረ ነገሮች ሲያንሱ

ሰውነት ያለአግባብ መክሳት

የተለያዩ የጤና ችግሮች

በአግባብ አለመመገብ እና የምግብ አበላል ችግሮች

ብዙ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማረግ

የወር አበባ በጣም ቀደም ብለው ወይም በጣም ዘግይተው ከሆነ ከሐኪምዎ ጋር መነጋገር በጣም ይመከራል። ይህ እንዳይሆን በቪታሚኖች የበለፀገ ምግብን መመገብ፣ ስኳር እና ጣፋጭ መጠጦችን ከመውሰድ መገደብ፣ ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ የጭንቀት መጠንን ለመቀነስ መሞከር፣ BMI ማስተካከል እና ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለማስወገድ ሰውነትን በሚገባ መንከባከብ አስፈላጊ ናቸው።