የሴት ለማህፀን ጤንነት ለመደገፍ ምን መብላት አለብኝ?

የማህፀን ጤንነት ብዙ ጊዜ አይወያይም ፤ ነገር ግን የሴቶች ጤና በጣም አስፈላጊ ገጽታ ነው ። ማሳከክ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ሽታ ያላቸው ፍሳሾች ሽፍታዎች በብዛት የሚስተዋሉ ችግሮች ቢሆኑም ስለማህፀን ጤንነት በብዛት ሲወራ አናስተውልም ነገር ግን ለ ሴት ልጅ ጤንነት ወሳኝ ነው።የማህፀን ችግሮች ምቾትን መንሳት በራስ መተማመንን መቀነስ እንዲሁም የለት ተለት እንቅስቃሴንም ሊያስተጓጉል ይችላል።ስለዚ ዛሬ ለማህፀን ጤንነት ጠቃሚ የምንላቸውን የምግብ አይነቶች አብረን እናያለን። 

  1. እርጎ

ማህፀን በተፈጥሮ ጤናማ ባክቴሪያዎች አሉት ይህ ደግሞ በሽታ አምጪ ከሆኑ ከውጪ ከሚገቡ ባክቴሪያዎች ይከላከላል።የእነዚህን ጠቃሚ ባክቴሪያዎች መጠን አርጎን በመመገብ መጨመር ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ እርጎ የማህፀን አካባቢን አሲዳማነት በመጨመር ኢንፌክሽንን ይከላከላል ካለም በቶሎ እንዲድን ይረዳል።

  1. ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች

እንደ ቆስጣ ጎመን የመሳሰሉ አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አታክልቶች በ ናይትሬት የበለፀጉ በመሆናቸው የማህፀንን የደም ዝውውር በመጨመር ድርቀት, ማሳከክ እና የማቃጠል ስሜትን ይከላከላል አብዛኛው ፍራፍሬዎች ደግሞ በውስጣቸው ከፍተኛ አንቲኦክሲዳንት ስላላቸው የደም ዝውውርን በማፋጠን ለእርግዝና እንዲሁም ለጠቅላላ ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።በ ቫይታሚን ኢ እና ሲ የበለፀጉ ፍራፍሬዎች በተጨማሪ የማህፀንን እና የሽንት ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይረዳሉ።

ብዙ ፍራፍሬዎች የደም ፍሰትን ለማሻሻል፣የሴሎችዎን ጤንነት ለመጠበቅ እና በመራባት ውስጥ ሚና የሚጫወቱትን አንቲኦክሲደንትስ የያዙ ናቸው። ፍራፍሬዎች በቫይታሚን ኢ እና በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ናቸው ይህም የሴት ብልት ኢንፌክሽኖችን እና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል። Fruits like Avocados are rich in omega-3, vitamin B12, and potassium which is important in hormonal balance and assists in the healing and regeneration. 

  1. የቅባት እህሎች

የቅባት እህሎች እና ጥራጥሬዎች እንደ ኦሜጋ3 ያሉ ጤናማ ቅባቶች የበለፀጉ ናቸው። እንዲሁም ፋይቶኤስትሮጅንን ስሐያዙ የወር አበባን ኡደት ያስተካክላሉ በተጨማሪም ከወርአበበባ መቆም ጋር ተያይዘው ሚመጡ ምልክቶችን ሆርሞን በማስተካከል ይከላከላሉ። በተጨማሪም የያዙት ዚንክ ቫይታሚን ቢ ኢ እና ካልሺየም ማሳከክ ማቃጠል እና የመቆጣት ስሜትን ይቀንሳል። ስለዚህ እንደ ለውዝ አልሞንድ ተልባ የዱባ ፍሬ የመሳሰሉ የቅባት እህሎችን ምግባችን ውስጥ ማካተት ያስፈልጋል።   

በአመጋገብዎ ላይ እንደ ኦቾሎኒ፣ ለውዝ፣ የተልባ ዘሮች እና የዱባ ዘሮች ያሉ ዘሮችን እና ለውዝ ማከል አለብዎት።

  1. ውሃ

ውሀ ምግብ ባይባልም ነገር ግን ሰውነታችን ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያስወግድ በጣም ይጠቅማል እንዲሁም ድርቅትን ስለሚከላከል በቀን ከ 6-8 ብርጭቆ ውሀ እንድንጠጣ ይመከራል።