የእርግዝና የሽንት ምርመራ ምንድነው እና እንዴት እንጠቀም?
ልጅ ለመውለድ አስበሽ ይሆን? ለማወቅ መጠበቅ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል። አንዲት ሴት እርጉዝ ከሆነች በቶሎ አውቃ ጤንነቷን መከታተል እና አንዳንድ የአኗኗር ለውጦችን ማድረግ ይኖርባታል። እርጉዝ ልሆን እችላለሁ ብለሽ ካሰብሽ የቤት ውስጥ የእርግዝና ምርመራ ለመግዛት ጊዜው አሁን ነው!
የእርግዝና ሽንት ምርመራ ቀላል፣ በተመጣጣኝ ዋጋ በቤትሽ ምቾት ሆነሽ እርግዝናን አስቀድሞ ለማወቅ አስተማማኝ የሆነ መንገድ ነው። ይሁን እንጂ እያንዳንዱ የእርግዝና ሽንት ምርመራ በተለየ መንገድ ስለሚሰራ ስለዚህ ምርመራውን መቼ መውሰድ እንዳለብሽ እና ውጤቱን እንዴት እንደሚተረጉሚ መመሪያዎችን ማንበብ አስፈላጊ ነው።
እነዚህ ምርመራዎች በሽንት ውስጥ ያለ ሁመን ኮሪዮኒክ ጎዶቶሮፒን (hCG) የሚባል ሆርሞንን በመለየት ይሰራሉ። ይህን ሆርሞን ሰውነትሽ ማምረት ሚጀምረው ከተፀነሰ ከስድስት እስከ አስር ቀናት ውስጥ ፅንሱ በማህፀን ግድግዳ ላይ ሲተከል ጀምሮ ነው። ስለዚህ የቤት ውስጥ የሽንት ምርመራ ለማድረግ የመጀመርያው ጊዜ ፅንስ ከተፀነሰ 14 ቀናት በኋላ ነው፣ ነገር ግን ትክክለኛ የሆነ ውጤት ለማግኘት የወር አበባሽ ጊዜ ካለፈ በኋላ መጠበቁ ጥሩ ነው።
ምርመራውን ከመጠቀምሽ በፊት የምርመራውን ማብቂያ ቀን አረጋግጪ፣ ሁሉንም መብራርያ በጥንቃቄ አንብቢ እና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ሰብስቢ። የሰዓት ቆጣሪ፣ ጠፍጣፋ ወለል እና ምናልባትም ንጹህ እና ደረቅ የሽንት መሰብሰቢያ ዕቃ ያስፈልግሻል። የመሃልኛውን የሽንት ናሙና መጠቀም አስፈላጊ ነው ይህ ማለት መጀመሪያ ትንሽ ሸንተሽ ከዚያ የቀረውን ለናሙና ምጠቀም ማለት ነው። የትኛውንም የእርግዝና ምርመራ ብትገዢ የትክክለኛነት እድሎችን ለመጨመር ጠዋት ላይ መጠቀሙ ይመረጣል።
ምንም እንኳን የተለያዩ አይነት የእርግዝና የሽንት ምርመራዎች ቢኖሩም በትክክል ከተጠቀምናቸው 99 በመቶ ያክል ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ። እነሱን ለመጠቀም በቀላሉ ለሶስት ሰከንድ ያህል ሽንት የያዘው ኩባያ ውስጥ ምርመራውን ክተቺው፣ ከሙከራ መስመሩ በላይ እንዳታልፊ። የእርግዝና ምርመራውን በጠፍጣፋ እና ደረቅ ወለል ላይ የውጤት መስኮቱን ወደ ላይ አዙረሽ ያስቀምጪ። ውጤቱም ከአምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ዝግጁ ይሆናል። የተለያዩ የምርመራ ምርቶች የውጤት ጊዜ እና ውጤቱን የሚያሳይበት መንገድ ቢለያይም ለመገንዘብ ግን ቀላል ናቸው። መደመር ምልክት (+)፣ ሁለት መስመሮች ወይንም ደካማ አንድ መስመር ማለት እርጉዝ መሆንሽን ያሳያል። የመቀነስ ምልክት (-) ወይም አንድ መስመር እርጉዝ አይደለሽም ማለት ነው። እንዲሁም የቀለም ለውጥ እና እንደ “pregnant" ወይም "not pregnant” በመሳሰሉት መንገዶች ውጤቱ ሊታይ ይችላል።
አወንታዊ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው hCG በሽንትዎ ውስጥ ከመደበኛ በላይ በሆነ ደረጃ እንደተገኘ ሲሆን በተቻለ ፍጥነት በአቅራቢያሽ የሚገኘውን የጤና ተቋም በመጎብኘት ለጤናማ እርግዝና ቀጣዩን የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ እና ክትትል ጀመሪ። በቂ የ hCG ሆርሞንን ለማምረት የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ ውጤቱ አሉታዊ የሆነው ቀደም ተብሎ ምርመራው ተወስዶ ሊሆን ስለሚችል እርጉዝ ከሆንሽ እና አሁንም የወር አበባዎ ካላየሽ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደገና ምርመራውን ሞክሪ። ይሁን እንጂ የተሳሳተ አጠቃቀም፣ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎች እና መድሃኒቶች የሽንት እርግዝና ምርመራ ውስጥ የተሳሳቱ ንባቦችን ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ማረጋገጫ ለማግኘት ጤና ጣቢያን መጎብኘት እንዳትረሺ።
Medical Information Disclaimer
This information and content is not designed to and does not provide medical advice, professional diagnosis, opinion, treatment, or services to you or to any other individual. It is for providing general information for educational purposes only and is not a substitute for medical or professional care.
Sources:
[1] UpToDate