እርግዝናና በሰውነት ላይ የሚመጡ ለውጦች?

"ይህንን ያውቁ ነበር?" ያረገዘች ሴት ካላረገዘች ሴት የማህጸን ክብደት እና ርዝመት በ500-1000 እጥፍ እንደሚጨምር፡፡ ይህም ማለት ያለረገዘች ሴት የማህጸን ክብደት ወደ 60 ግራም ይመዝናል፡፡ ከ5-10 ml ድረስ ይይዛል እንዲሁም 7.5 ሳ.ሜ. ርዝማኔ ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን እርግዝና እየገፋ ሲሄድ ወደ 900-1000 ግራም ክብደት ይደርሳል፡፡ እስከ 35 ሳ.ሜ. ርዝማኔ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ 

በእርግዝና ወቅት አንዲት ሴት በተደጋጋሚ የሚመጡባት ጥያቄዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህም ለምን ይደክመኛል? ለምንስ ያቅለሸልሸኛል? ለምን የረሀብ ስሜት የሰማኛል? ለምን ይሆን ትንፋሽ የሚያጥረኝና የልቤ ምት ፍጥነት የጨመረው? ይህን ያህል ክብደት መጨመር ተፈጥሮአዊ ይሆን? የጡት ሕመምና መተለቅስ ለምን ይሆን? የቆዳ ሸንተረር ጠባሳዎች ይጠፋሉ ወይስ በሽታ ላይ ወድቄ ይሆን?

አትጨነቁ እነዚህ ሁሉ የሰውነት ለውጦች ተፈጥራዊና የሚጠበቁ ክስተቶች ናቸው፡፡ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች በፍጥነት ለሚያድገው ጽንስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ምክንያት ናቸው፡፡ ከሰውነታችን ለውጦች መካከል አንዱና የመጀመሪያው 12 ሳምንታት የሚታየው የጡት መጠን መተለቅ፣ ሕመም እንዲሁም ከጡት ጫፍ ወፍራምና ቢጫ ፈሳሽ ማየት ሲሆን በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ እርግዝና ያጋጠማት እናት ላይ ጎልቶ የሚታይ ይሆናል፡፡ እርግዝናው እየገፋ በመጣ ቁጥር በጽንሱ እድገት ምክንያት የማህጸን መተለቅና የመለጠጥ ባህሪ ይኖረዋል፡፡ ይህም ወደ ታች ወደ ሽንት ትቦ ስለሚለጠጥ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት እንዲሁም ወደ ላይ ወደ ሆድና ዳያፍራም መግፋት ምክንያት ትንፋሽ መቆራረጥና ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ይኖራል፡፡ በእርግጥ የሚያድገው ጽንስ የኦክስጅን መጠን ፍላጎት ከ20-40% ስለሚጨምር የትንፋሽ መጨመርና መድከም አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ 

ሌላው የክብደት መጨመር በእርግዝና ወቅት የሚጠበቅ ክስተት ሲሆን በመጀመሪያው ሳምንታት ግን በማቅለሽለሽና በማስመለስ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ምክንያት የኪሎ መቀነስ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሴት እርግዝና ከተከሰተ አንስቶ እስክትገላገል ድረስ ወደ 11 ኪሎ እስከ የያዘችው ጽንስ አካትቶ የመጨመር ይኖራል፡፡ በእርግዝና ክትትል ወቅት የኪሎ ክትትል ወሳኝና አስፈላጊ ሲሆን ምክንቱም ያለአግባብ መጨመር ወይም መቀነስ ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚመጡ በሽታዎች ምክንያት ስለሚሆን እነዚህም እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት፣ የማህጸን ውስጥ የጽንስ መቀጨጭ ወ.ዘ.ተ. ናቸው፡፡

በእርግዝና ወቅት የሚመጡ የቆዳ ሸንተረር ጣባሳዎች በቆዳችን ላይ እንደ ቡኒ፣ ጥቁር በተለይም በሆዳችን፣ በጡታችንና ጭኖች መካከል ይታያሉ፡፡ እንዲሁም አልፎ አልፎ በፊታችን ግንባርና ከዓይን ስር ይወጣሉ፡፡ ይኸው በውስጣችን የሚገኘው የአልዶስትሮን ሆርሞን መጨመር ምክንያት ነው፡፡ የሰውነት ክብደት መጨመርና መለጠጥ ሌላኛው መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ የቆዳ ሸንተሮሮች እርግዝናው ካበቃ ወዲህ በመደብዘዝና የመጥፋት ሂደት ይታይባቸዋል፡፡ በእርግዝና ወቅት ሌሎች የማናስተውላቸው ነገር ግን የሚታዩ ለውጦች እንደ ፀባይ መቀያየር፣ መከፋት፣ እንዲሁም የፀጉር መነቃቀልና ማነስ በኤስትሮጅን በከፍተኛ መጠን መጨመር ምክንያት ይሆናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ለውጦች አንዲት ሴት ወደ እናትነት የምታሳልፋቸው የተፈጥራዊ ጉዞ ናቸው፡፡ 

ሌላው በእርግዝና ወቅት የምናየው ነገር ክብደት መጨመር ነው ። በሽተኛው በማቅለሽለሽና በማስመለስ ምክንያት በሚኖረው ክብደት ልክ በሳምንቶቹ መጀመሪያ ላይ መቀነስ አለበት ። ይሁን እንጂ በቀጣዮቹ ወራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ክብደት ይኖራቸዋል ። በነጠላቶን (1 ሽሉስ) የእርግዝና ጊዜ ጠቅላላ ክብደት ሽሉ ፣ ማህፀን ፣ የእንግዴ ልጅ እና ወዘተ ከ11 ኪሎ ግራም በላይ ነው... ክብደት የመከታተል ሂደት ወሳኝ ክፍል ነው ። ከመጠን በላይ መወፈር ወይም ከመጠን በታች የመወፈር ወይም ከክብደት ጋር የተያያዘ የእርግዝና ምልክት ሊሆን እንደሚችል እንደ ቅድመ ማቅድመምባሲያ (የደም ግፊት) ፣ የስኳር በሽታ እና ኢንስትራክተር የክብደት ክልከላ ወይም በፋስቱ እድገት ስር መሆናቸውን ለይቶ ማወቅ ወቅትና መደበኛ መሆን አለበት ።

የኤስትሮጂን እና የስትሮጅን መጠን መጨመር በቆዳችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ። በፊት ፣ በዓይን እና በግንባር አካባቢ እንደ "ክሎዛማ" (የእርግዝና መከላከያ ጭንብል) ያሉ ለውጦችን እናስተውላለን ፤ ይህም አብዛኛውን ጊዜ ከወሊድ በኋላ ይወገዳል ። "ስትሪያ ስቲዳሩም" ሌላው በቆዳ ላይ የተደረገ ለውጥ ነው ። እነዚህ ምልክቶች በቆዳው ላይ እንደ ቡናማ እና ጥቁር ቀለም የሚገለጡት ሆድ ፣ ጡት እና ጭን የተለያየ ርዝመት እንዳላቸው ነው ። በእርግዝና ወቅት በሚጨምረው በእነዚህ ምልክቶች ውስጥ አልዶስተሮን ተብሎ የሚጠራው ሆርሞን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ። ይሁን እንጂ በቆዳ ላይ በሚንሳፈፍበት ጊዜ የሚከሰት ነገርም አለ ። ከመጠን ያለፈ ክብደት ስለሚኖረው ይህ ሁኔታ ጤናማ እንዳልሆነም ማስታወስ ይኖርብናል ።

በተጨማሪም እንደ ኤስትሮጂን ካሉ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የኤስትሮጂኖች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የተለመዱ ለውጦች ናቸው ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንደ ፀጉር መርገፍ ያሉት ሁኔታዎች እምብዛም አይከሰቱም ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ተፈጥሯዊ ክስተቶች እና እያንዳንዷ ሴት የምትለማመዳቸው ወደ እናትነት የሚጓዙ ናቸው ፡ ፡ 

ያለጊዜው የሚመጣ የሆድ ቁርጠት፣ ከማህጸን ደም መፍሰስ፣ ወደ ታች መግፋት፣ አለአግባብ ማስመለስና ምግብ አለመርጋት፣ ከመጠን በላይ ኪሎ መጨመር ወይም መቀነስ ካለ ወደ ሕክምና በአፋጣኝ ሄዶ ሐኪሞትን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በእግዝና ወቅት የሚከሰቱ የሰውነት ለውጦች ላይ የነበረን አጭር መግለጫ ሲሆን ለበለጨ ዝርዝር መረጃ www.yenehealth.com ይጎብኙ፡፡