ሚመጡ ችግሮች ምክንያት የሚከሰት ሞት ከአስር እናት ውስጥ ሶስቱን በጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የእንደሚያጠቃ ታውቃላችሁ?
ጽንስ ማቋረጥ የምንለው፡ ጽንሱ ተወልዶ ለመኖር የሚችልበት ደረጃ ላይ ሳይደርስ እርግዝና የመቋረጥ ሂደት ነው፡፡ ይህም በኛ ሃገር 6ኛው ወር አካባቢ ድረስ ነው። ጽንስ የማቋረጥ ሂደት ያለምንም ምክንያት ሊከሰት ሲችል ይህም በተለምዶ ‹‹የጽንስ መጨንገፍ›› ተብሎ ሲጠራ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ኢንዲዉስድ›› ብለን የምንጠራው ደግሞ በህክምናመንገድ ጽንስ የማቋረጥ ሂደት ሲደረግ ነው፡፡
ጥንቃቄ የጎደለው የጽንስ ማቋረጥ ሂደት ማለት በሂደቱ በቂ ስልጠናና ልምድ በሌላቸው፤ የጤና ባለሙያዎች ባልሆኑ ሰዎች እንዲሁም ትክክለኛ መሳሪያዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲደረግ ሲሆን እንደኛ ባሉት ታዳጊ ሃገራት በዚህ አይነት መልኩ የሚደረጉ ጽንስ የሟቋረጥ ሂደቶች ከግማሽ በመቶ በላይ ናቸው። በጽንስ ማቋረጥ በኩል በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ከጊዜና ከትክክለኝነት አንጻር ብዙ ክርክሮች ሲኖሩ በኛ ሀገር ግን በመጀመሪያዊች አራት ወራት ጊዜ ውስጥ በህግ የተፈቀዱትን መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ ጽንስ ማቋረጥ ይፈቀዳል።
ለጽንስ ማቋረጥ ወይም ውርጃ የሚያጋልጡ ነገሮች፡
ለጽንስ መቋረጥ ሊያጋልጡ የሚችሉ የተለያዩ ሁኔታዎች ሲኖሩ፤ እነዚህም በአፍሪካ ውስጥ ለሚደረጉት ጥንቃቄ የጎደላቸው የጽንስ ማቋረጥ ሂደቶች ቀዳሚውን ድርሻ የሚይዘው ያልተፈለገ ወይም ያልተጠበቀ እርግዝና መኖር በዋናነት ይጠቀሳል። እንዲሁም የዘረ-መል ችግሮች በሚኖሩበት ሰዓት፣ከ35 ዓመት ዕድሜ በላይ የሚከሰት እርግዝና፣ከዚህ በፊት የተከሰተ የጽንስ መጨንገፍ መኖር፣ of miscarriages, ባለፉት እርግዝናዎች ላይ በተከታታይ የጽንስ መጨንገፍ ያጋጠማቸው ሴቶች ፣የማህጸን እና የማህጸን በር ችግሮች መኖር፣ ሲጋራና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች ጎጂ መድሃኒቶችን መጠቀም፣ ከሚፈለገው በላይ ክብደት ማነስ ወይም ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሌሎቹ አበይት ምክንያቶች ናቸዉ።
በጽንስ ማስወረድ ምክንያት የሚመጡ አምሥት ዋና ዋና ችግሮች
በጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የሚመጡ ችግሮች ምክንያት የሚከሰት ሞት ከ10 ውስጥ ሶስቱን እንደሚያጠቃ ታውቃላችሁ? ይህ በሁሉም የዕድሜ ክልል፤ ዘር፤ ትምህርት ደረጃ እና የትዳር ሁኔታ ያሉት ሴቶች ላይ ሊከሰት ይችላል።እነዚህ ችግሮች በተለይ በጥንቃቄ በጎደለው የጽንስ ማቋረጥ ጊዜ በብዛት የሚከሰቱ ሲሆኑ እነዚህም
ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ፤ ይህም ከጾታዊ አካላት ላይ የሚደርስ ጉዳት ወይም ከውርጃው በኋላ ማህጸን መኮማተር ሲያቅተው ወይም ሌላ ከደም ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት ሊከሰት ይችላል ይህ ደም መፍሰስ ከፍተኛ የሆነ ደረጃ ላይ በመድረስ ደም መሰጠት ሊያስፈልግ ይችላል።
ኢንፌክሽንና የደም መበከል ሊከሰት የሚችል ሲሆን ይህም በራሱ በሚፈጠርም ይሁን በመሳሪያ የሚደረግም ላይ ሊከሰት ይችላል።ይህ የሚፈጠርበት አንደኛው ሁኔታ ከውርጃ በኋላ ማህጸን ውስጥ የሚቀር የፅንስ አካል ሲኖር ወይም ለጽንስ መቋረጥ የተጠቀሙበት መሳሪያ የተበከለ ከሆነ ነው።
Retained products of the fetus (similar to above) this can present as abdominal pain, fever, blood in stool, nausea and vomiting.
የአንጀት ጉዳት መኖር ይህ በሚኖርበት ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የሆድ ህመም፣ ትኩሳት፣ ደም የተቀላቀለበት ሰገራ እንዲሁም ማቅለሽለሽና ማስመለስ ሊኖር ይችላል ።ተያይዞም የፊኛ መጎዳት ሊኖር ስለሚችል ይህም ፊኛ አካባቢ የሚኖር ህመምና ከሽንት ጋር ደም መቀላቀል ሊያሳይ ይችላል
መሃንነት እና በሚቀጥሉት እርግዝናዎች ላይ የልጁ ያለዕድሜ መወለድ፤ ይህም በተያያዝነት የሚወለደው ህጻን ላይ የሚኖር የአዕምሮ እድገት ችግሮች እንዲሁም ሞትን ሊያመጣ ይችላል።
የስነ-ልቦና ችግሮች ሌላኛው ከፍተኛ ተጽዕኖ በእናትየው ላይ የሚያስከትል ሲሆን፣ ይህም ከድባቴ እስከ ሱስ መጠቀምና ራስን ለማጥፋት መገፋፋት ድረስ ሊደርስ ይችላል። በማንኛውም ጊዜ ከጽንስ ማቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ የደም መፍሰስ፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፤ የሆድ ህመም፣ ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ መኖር፣ ከሽንት ወይም ሰገራ ጋር ተያይዞ ደም መቀላለል ሲኖር ፈጥኖ የጤና ባለሙያን ማማከርያስፈልጋል። በተጨማሪም እርግዝና ከታወቀ በኋላ ማስወረድ አስፈላጊም ከሆነ በመጀመሪያ የጤና ተቋማት ጋር በመሄድ ባለምክንያቱም ያሉትን ነገር አውቆና የሚጠቅመውን ውሳኔ የመወሰን መብት አለሽ ባለሙያ ማማከር መሰረታዊ ነው።
Medical Information Disclaimer
This information and content is not designed to and does not provide medical advice, professional diagnosis, opinion, treatment, or services to you or to any other individual. It is for providing general information for educational purposes only and is not a substitute for medical or professional care.
Sources:
[1] WHO
[2] ACOG
[3] UpToDate