ሁለት የወሊድ መንገዶች አሉ. እነዚህም በምጥ መውለድ እና በቀዶ ጥገና መውለድ ናቸው።

በምጥ መውለድ ማለት በእናቲትዋ የወሊድ አካላት ሕፅኑን የማስወጣት ሂደት ነው። ይህ የወሊድ ዘዴ የሚከናወነው ምጥ ከጀመረ በኋላ ነው. ምጥ የሚያመለክተው ህፃኑን ለማስወጣት ማህፀኑ መኮማተር መጀመሩን ነው. ምጥ የሚወስደው ጊዜ ከሴት ሴት ሊለያይ ይችላል. ምጥ በራሱ ሊጀምር ይችላል ወይም ለመጀመር እንደ መድሃኒት ያሉ ሌሎች ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል. ምጥ በሚጀምርበት ጊዜ የማኅጸን የታችኛው ክፍል የሆነው የማኅጸን ጫፍ መከፈት ወይም መስፋት ይጀምራል. ይህ መስፋት ከ 1 እስከ 10 ሴ.ሜ ሊለካ ይችላል. የማኅጸን ጫፍ 10 ሴ.ሜ ሲደርስ እናትየው ህፃኑን በብቃት ለመውለድ እንድትገፋ ይጠበቅባታል።

የምጥ መውለድ በመሳሪያ በመታገዝ ሊከወን ይችላል. በመሳሪያ የታገዘ ወሊድ ኦፕሬቲቭ የወሊድ ዘዴ በመባልም ይታወቃል፣ ህፃኑን ለማውጣት መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ይህ ዘዴ የሚመረጥበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ ነገር ግን በአጠቃላይ ህፃኑን በፍጥነት መውለድ በሚያስፈልግበት ጊዜ እና የእናቲቱ እና የሕፃኑ ሁኔታ ሲፈቅድ ይከናወናል:: ኢፒዚዮቶሚ ወይም ስቲች ለህፃኑ መዉጫ ለማስፋት የሚደረግ ቅድ ነዉ:: የሕፃኑን መወለድ ተከትሎ የሚሰፋ ይሆናል::

በቀዶ ጥገና መውለድ በሆድ በኩል ልጅን የየማስወጣት ዘዴ ነው:: ሕፃኑን ለማውጣት የተለያየ የሆድ ክፍልን በመቅደድ ይከናወናል:: በቀዶ ጥገና ለመውለድ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ:: በአጠቃላይ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በምጥ መውለድ በማይቻልበት ጊዜ ይከናወናል። ታቅዶ ወይም በድንገተኛ ሁኔታ ሊከናወን ይችላል:: የድንገተኛ ቀዶ ጥገና የሚከናወነው ምጥ ከጀመረ በኋላ ውስብስብ ችግሮች ሲፈጠሩ ወይም የሕክምና ሁኔታዎች የሕፃኑን ወይም የእናትን ህይወት አደጋ ላይ ሲጥሉ ነው::

በምጥ ከመውለድ ጋር ሲወዳደር በቀዶ ጥገና መወለድ ከደም መፍሰስ፣ ከኢንፌክሽን፣ ከሆስፒታል ቆይታ እና ከማገገም ጊዜ መጨመር እና ከማደንዘዣ ጋር የተያያዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር የተያያዘ ነው። ነገር ግን በትክክለኛ ምክንያቶች ሲሰራ ለእናቲቱም ሆነ ለህፃኑ ህይወትን ሊያድን ይችላል::