ፓፕ ስሚር ምንድነው፡ በምን ያህል ግዜ መመርመር አለብን?

Pap smear የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ አይነት ሲሆን፤ ከማህፀን ጫፍ ላይ በቀላል መንገድ ናሙና በመውሰድ ካንሰር ህዋስ መኖራቸውን እና አለመኖራቸውን በላባራቶሪ የሚያሳይ የምርመራ መንገድ ነው። ይህም ቴስት የቅድመ ካንሰር ለውጦችን በማግኘት በካንስር የመያዝ እድልን የሚያመላክት ሲሆን፤ እኚህን ለውጦች ከተገኙ ደግሞ ቀደም ብሎ ህክምና እንዲደረግ ያስችላል። 

-- ትክክለኛውን የምርመራ ውጤት ለማግኘት ትክክለኛ ዘዴ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ናሙናውን ለማግኘት የማኅጸን ጫፍን በንፁህ ስፔኩለም ማየት (ይህም ማለት ማህፀንን ውጫዊ ክፍልን ለማየት የሚያስችል መሳሪያ በመጠቀም) እናያለን። የማኅጸን ጫፍ ውጫዊ ክፍል ከተፀዳ በኋላ ናሙናውን (sample) ለመውሰድ ሚያስችል ብሩሽ በመጠቀም የማኅጸን ጫፍ ውጫዊ እና ውስጣዊ ህውሀሶችን 360 ዲግሪ ብሩሹን በማዞር ይወሰዳል። የተወሰደውን ናሙና በማይክሮስኮፕ በስነደዌ ሀኪም(pathologist) ካንሰር ህዋስ ወይም HPV infection መኖሩን ወይም አለመኖሩን ይረጋገጣል።

ምርመራው ውጤታማ እንዲሆን ከምርመራው በፊት የሚከተሉትን ማድረግ አስፈላጊ ነው። 

  • ይህ ምርመራ በውር አበባ ወቅት ባይደረግ ይመረጣል።
  • ከምርመራው ሁለት ቀናት በፊት ግንኙነት አለማድረግ፣ የሴት ብልትን አብዝቶ አለመታጠብ እና ማንኛውንም በማህፀን የሚደረጉ የወሊድ መከላከያ ጋር የተገናኙ መድኃኒቶችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል።

ከ21-65 አመት እድሜ ክልል ውስጥ ያለች ሴት የማኅጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማድረግ ሲኖርባት ምርመራው ለብቻው ከተሰራ በየ3 አመት፤ ከ HPV DNA test ጋር ከሆነ ደሞ በየ 5 አመት ልዩነት መደረግ አለበት። የተለያዩ በሽታ ያላቸው ሰዎች በአጭር ግዜ ልዩነት ውስጥ ምርመራውን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ለምሳሌም የHIV ታማሚዎች ከሆኑ ግንኙነት በጀመሩ ጊዜ ጀምሮ ቅድመ ካንሰር ምርመራውን 21 አመት እድሜን መጠበቅ ሳይኖርባቸው በአጭር interval ማከናወን ይኖርባቸዋል። ይህም የሚመከረው ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ልዩ ተጋላጭነት ስለሚኖራቸው ነው።

ይህንን ምርመራ በሰለጠኑ የጤና ባለሞያዎች የሚሰራ ሲሆን በብዙ የህክምና ቦታዎች ላይገኝ ይችላል።

በምርመራው ወቅት ጤነኛ ህውሀሶች ብቻ ከተገኙ እስከሚቀጥለው ምርመራ ቀጠሮ ያለምንም ስጋት መጠበቅ ይችላሉ። ነገር ግን የተመረመረው ናሙና ከተለመደው ውጪ or abnormal cell ውጤት የሚያሳይ ከሆነ የህክምና ባለሞያ በተለየ መሳሪያ ተጨማሪ የባዮፕሲ ምርመራ በማድረግ ካንሰር መኖሩን ያረጋግጣል። ልብ ማለት ሚያስፈልገው ፖዘቲቭ ውጤት ነው ማለት የማህፀን ጫፍ ካንሰር አልዎት ማለት እይደለም።

ለተጨማሪ መረጃ ዶክተርዎን ያማክሩ።