ፍቃድ በግንኙነት ጊዜ የሚለው ርዕስ የሚያስረዳን ፍቃድ ማለት አንድ ሰው የሌላውን ሀሳብ ወይም ፍላጎት በራሱ ተነሳሽነት ያለምንም ተጨማሪ ተፅዕኖ ቢስማማ ነው። እንደ ህክምና ፣ ህግ ፣ ጥናት እና ምርምር እና የግብረስጋ ግንኙነት ባሉ ዘርፎች ዙሪያ አገልግሎት ላይ ሲውል የተለየ አውዳዊ ትርጓሜ ያለዉ ግን የተለመደ የንግግር ቃል ነው።

ፍቃድ በግንኙነት ጊዜ የሚለው ርዕስ የሚያስረዳን ፍቃድ ማለት አንድ ሰው የሌላውን ሀሳብ ወይም ፍላጎት በራሱ ተነሳሽነት ያለምንም ተጨማሪ ተፅዕኖ ቢስማማ ነው። እንደ ህክምና ፣ ህግ ፣ ጥናት እና ምርምር እና የግብረስጋ ግንኙነት ባሉ ዘርፎች ዙሪያ አገልግሎት ላይ ሲውል የተለየ አውዳዊ ትርጓሜ ያለዉ ግን የተለመደ የንግግር ቃል ነው።ወሲባዊ ፍቃድ ማለት በማንኛውም ወሲባዊ ድርጊት ውስጥ ለመሳተፍ የሚሰጥ የፍቃድ አይነት ነው። በወሲባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በምትሳተፉበት ጊዜ ፣ ፍቃደኝነት ስለ ግንኙነት ነው እና ለእያንዳንዱ አይነት እንቅስቃሴ በእያንዳንዱ ጊዜ መከሰት አለበት ።ስምምነት እና ፍቃድ መጠየቅ የግል ድንበሮችን ስለማስቀመጥ፣ አጋርዎን ስለማክበር እና ነገሮች ግልጽ ካልሆኑ ማረጋገጥን የሚያስረዱ ቃላት ናቸው። ሁለታችሁም ስለምትፈልጉት ነገር በግልጽ ማውራት እና ድንበሮችን ማበጀት በማንኛውም ግንኙነት (ጊዜያዊም ሆነ የረጅም ጊዜ) አስፈላጊ ነው።

ስምምነት፡- ግልጽ፣ ቀጣይነት ያለው፣ ወጥነት ያለው እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። -

  • ቻ ጥሩ አይደለም። አንዲሁም "አይ" የሚለው ቃል አለመኖር ፍቃድ ተሰጥቷል ለማለትም በቂ አይደለም።
  • ስምምነት ቀጣይ ነው ማለት በእያንዳንዱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ደረጃ ላይ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ፈቃድ ሊኖርዎት ይገባል ማለት ነው። ፈቃዱ በማንኛውም ጊዜ ሊወገድ እንደሚችል ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። ደግሞም ሰዎች ሐሳባቸውን እንደሚለውጡ መገንዘብ ይገባል።
  • ፈቃድ በውዴታ ነው ማለት በነጻ እና በውዴታ መሰጠት አለበት። ውሎ አድሮ አዎ አይደለም እስኪል ድረስ አንድ ሰው ወሲባዊ ድርጊት እንዲፈጽም ደጋግሞ መጠየቅ፣ መገደድን ነው የሚያሳየው። በቁርጠኝነት ግንኙነት ውስጥ ያሉ ወይም ያገቡ ሰዎችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ፈቃድ ያስፈልጋል። ማንም ሰው ማድረግ የማይፈልገውን ነገር የማድረግ ግዴታ የለበትም, እና በግንኙነት ውስጥ መሆን አንድ ሰው በማንኛውም አይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ውስጥ እንዲሳተፍ አያስገድድም.
  • ስምምነት ወጥነት ያለው ነው ማለት እያንዳንዱ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ውስጥ ያለ ተሳታፊ ፈቃዱን መስጠት መቻል አለበት። አንድ ሰው በጣም የሰከረ እንዲሁም በአልኮል ወይም በአደገኛ ዕፆች የተዳከመ ከሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ ካልነቃ፣ ፈቃድ የመስጠት አቅም የለውም። ሌላው ሰው ለመስማማት በጣም የተዳከመ መሆኑን አለመገንዘብ እና መቀጠል ወሲባዊ ጥቃት ነው።በተጨማሪም፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈቃድ ዕድሜ አንድ ሰው ለጾታ ግንኙነት ፈቃድ ለመስጠት በሕጋዊ መንገድ የሚፈቅድለትን ዕድሜ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ከስምምነት ዕድሜው በታች ከሆነ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸሙ ትልልቅ ሰዎች የእስር ጊዜ ይጠብቃቸዋል እንዲሁም እንደ የወሲብ ጥፋተኛ ይመዘገባሉ።
  • ፈቃድ መጠየቅ አጠቃላይ ስሜትን ገዳይ ነው ብለው ሊጨነቁ ይችላሉ፣ነገር ግን ያለው አማራጭ - ፍቃድ ባለመጠየቅ የሆነ ሰው ላይ ወሲባዊ ጥቃት ያደርሳሉ - ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም!
  • ስለ ፍቃድ ለመነጋገር መንገዶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
    • እችላለሁ…?
    • ስለ ፍቃድ ለመነጋገር መንገዶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- እችላለሁ…? ወሲብ መፈጸም ትፈልጊያለሽ/ ትፈልጋለህ?

ያለፈቃድ፣ ማንኛውም አይነት ወሲባዊ ድርጊት (መነካካት፣ መሳም እና ግንኙነትን ጨምሮ) ወሲባዊ ጥቃት ነው። እንደ አስገድዶ መድፈር፣ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ እና ወሲባዊ ጥቃት ይቆጠራል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጾታዊ ጥቃት ከአምስቱ ሴቶች አንዷን ይጎዳል፤ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከፍተኛ የህብረተሰብ ጤና እና የሰብአዊ መብት ችግር ነው።