ምድቦች: Maternal and Nursing
አጋራ

የድህረ ወሊድ ወቅት አንዲት እናት ከወለደችበት ሰአት አንስቶ ከእርግዝና ቀደም ወደነበረው አቋሟ እስከምትመለስ ድረስ ያለዉን ጊዝ ያጠቃልላል። ይህ ወቅት አብዛኛውን ጊዜ ከ 6-8 ሳምንት ይቆያል፡፡

በዚህ ወቅት ብዙ አካላዊ እና ስሜታዊ ለውጦች ይኖራሉ፡፡ ለእናትነት አዲስ እንደመሆንሽ በርካታ አዳዲስ ነግሮች ያጋጥሙሻል፡፡ በመጀምሪያወቹ ሳምንታት ብዙ እረፍት ማድረግ፣ አመጋገብን ማሰተካከል እንዲሁም የሰዎችን እርዳታ ማግኘት ያስፈልግሻል፡፡ ይህም ራስሽን በመንከባከብ ጥንካሬሽን ለማጎልበት ይረዳሻል፡፡

1. የደም መፍሰስ

በድህረ ወሊድ ጊዜ ከማህፀን የሚወጣው ፈሳሽ Lochia ይባላል፡፡ ከ 4- 8 ሳምንት የሚቆይ ሲሆን መጠኑ በየቀኑ እየቀነሰ የሚሄድ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያወቹ ቀናት ፈሳሹ የወር አበባ በሚበዛበት ወቅት ከሚወደው መጠን ጋር ይመሳሰላል፡፡

በ2-4 ቀናት ውስጥ ወደ ውሃማ ወይም ፈዘዝ ያለ ቀይ ቀለም ይለወጣል፡፡ ይህ ፈሳሽ እየቀነሰ ሄዶ በ10 ቀናት ውሰጥ ትንሽ መጠን ያለው ውሃማ ወይንም ቢጫ ፈሳሽ ይሆናል፡፡ በተክታዮቹ 2-4 ሳምንታት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይቆማል፡፡ ከዚህ የተለየ ወይንም የጨመረ ደም መፍሰስ ካጋጠመሽ ባፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብሻል፡፡

*

2. You will have mood changes

ከዚህ ብፊት የማያሰጨንቁሽ ነገሮች ይበልጥ አሳሳቢ ሆነው ሊታዩሽ ይችላሉ፡፡ ይህ የስሜት መለዋወጥ (Baby blues) ከወሊድ በኋላ እስከ 80% እናቶች ላይ ይከሰታል፡፡ ምልክቶቹም ሀዘን፣ ድካም እና የጭንቀት ስሜት ሲሆኑ በሳምንታት ውስጥ የሚጠፉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጣም ክባድ ሀዘን ፣ ጭንቀት፣ ብዙ ማልቀስ፣ የእንቅልፍ መረበሽ፣ የጥፋተኝነት ወይም ዋጋ የለሽነት ስሜት ከተሰማሽ ይሄ የድህረ- ወሊድ ድባቴ(Post-partum depression ) ምልክቶች ስለሆኑ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይኖርብሻል፡፡

*

3. እንቅልፍ ማጣት

ማታ ማታ ልጅሽን ለማጥባት በተደጋጋሚ ከ3-4 ጊዜ ከ እንቅልፍሽ ትነቂያለሽ፡፡ በመሆኑም ቀን ቀን ልጅሽ በሚተኛበት ጊዜ አብረሽ ለመተኛት ሞከሪ፡፡ ምንም እንኳን ለ አጭር ደቂቃዎች ብትተኝም ባጠቃላይ ጥሩ እረፍት እንድታገኝ ይረዳሻል፡፡

4. 4. ሠውነት ከእርግዝና በፊት ወደነበረው አቁሙ ወዲያውኑ አይመለስም

ብዙ እናቶች በእርግዝና ወቅት የጨመሩትን ክብደት በፍጥነት መቀነስ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ጡት በማጥባት ላይ ከሆንሽ አላግባብ የሆነ ምግብ መቀነስ ወይንም በፍጥነት ብዙ ኪሎ መቀነስ አንቺንም ሆነ ልጅሽን ይጎዳል፡፡ ወደ ቀድሞው ክብደትሽ ለመመለስ ብዙ ወራት ሊያሰፈለግሽ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ስብ ያላቸውን ምግቦች መቀነስ እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በብዛት መመገብ የተመጣጠነ ምግብ መብላት እና ዉሀ በብዛት መጠጣት ይጠቅምሻል፡፡ ጡት በምታጠቢበት ጊዜ ለሚኖር የውሃ ጥም ውሃ እና ወተት መጠጣት ጥሩ ምርጫዎች ናቸው፡፡
*

5. ሽንት ቤት በምትጠቀሚበት ጊዜ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል

ሽንትሽን በምትሸኝበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ ስፌት (Stich) ካለ ደግሞ ህመሙ የባሰ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሆድ ድርቀት እና ኪንታሮት ከወሊድ በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ለብ ባለ ውሀ ወይም በቀዝቃዛ ውሀ ለተወሰኑ ደቂቃዎች መቀመጥ (Sitz bath) የህመም ስሜቱን በእጅጉ ይቀንሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ዉሃ መጠጣት፣ መንቀሳቀስ እነዲሁም መድሃኒቶችን በመጠቀም የሆድ ድርቀትን ማሻሻል ይቻላል፡፡ ነገር ግን ማንኛውንም መድሀኒት ከመውሰድሽ በፊት የህክምና ባለሙያ ማማክር ይኖርብሻል፡፡

6. ራስ ምታት

ራስ ምታት እሰከ 40% በሚሆኑ እናቶች ላይ ከወሊድ በኋላ ይከሰታል፡፡ መንስኤው የእንቅልፍ እጦት፣ ጭንቀት፣ የሰመመን መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ወይም ከሰውነት ለውጦች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ወቅት የሚከሰት ራስ ምታት አብዛኛውን ጊዜ አደገኛ ባይሆንም የደህረ-ወሊድ ደም ግፊት(Post-partum preeclampsia) ምልክት ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

7. የፀጉር መነቃቀል

በእርግዝና ወቅት በ ሆርሞኖች ምክንያት የፀጉር መብዛት/መፋፋት የሚኖር ሲሆን ከወሊድ በኋላ ግን የሚነቃቀል ይሆናል፡፡

8. የወር አበባ በድጋሚ ሳይመለስ ልታረግዢ ትቸያለሽ

የወር አበባ የሚመለስበት ጊዜ በጡት ማጥባት ላይ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ጡት የማያጠቡ እናቶች ከ6-8 ሳምንት ባለው ጊዜ ውሰጥ የወር አበባ ሊያዩ ይችላሉ፡፡ የሚያጠቡ ከሆነ ከ9-18 ወር ሊቆይ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ጡት የሚያጠቡ እናቶች የወር አበባ የሚያዩበት ጊዜ የራቀ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጡት ማጥባትን እንደ እርግዝና መከላከያ ዘዴ መጠቀም አይመከርም፡፡ ጡት እያጠባሽም የወር አበባሽ ከመመለሱ በፊት እረግዝና ሊከሰት ይችላል፡፡

*