የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ መቼ እና ለምን መደረግ አለቦት?

የማኅጸን ጫፍ የማኅጸን የታችኛው ክፍል ሲሆን በአካባቢው የካንሰር እብጠት ሊከሰት ይችላል። በኢትዮጵያ የጡት ካንሰርን ተከትሎ በሴቶች ላይ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ካንሰር ሲሆን 90በመቶ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የሚከሰተው በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን (HPV 16 እና/ወይም 18) በተባለ የቫይረስ ጋር የተያያዘ ነው። አንዳንዶቹ የአደጋ መንስኤዎች በለጋ እድሜ በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ በርካታ ልቅ የሆኑ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አጋሮች፣ ከዚህ በፊት የአባላዘር በሽታ ታሪክ ከነበረ፣ የሰውነት የበሽታ የመቋቋም ሁኔታዎችን የሚቀንሱ ነገሮች (ኤችአይቪ ኢንፌክሽን፣ ድህረ-ንቅለ ተከላ) እና ሲጋራ ማጨስ እና/ወይም ለሁለተኛ እጅ ማጨስ መጋለጥን ያካትታሉ። 

የበሽታው ከ35-44 እድሜ ውስጥ ያሉትን የሚያጠቃ ሲሆን የተጠቁ ሴቶች ለብዙ አመታት ምንም አይነት የህመም ምልክት አይታይባቸውም። ነገር ግን የካንሰር ደረጃ ላይ ሲደርስ ከማኅጸን ጫፍ ጠረን ያለው ደም መፍሰስ በተለይም ከግንኙነት በውሀላ ፣ በዳሌ አካባቢ እና በታችኛው ጀርባ አካባቢ ህመም እና ከተስፋፋም በመጨረሻ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል። ስለዚህ ለአብዛኛዎቹ ታካሚዎች በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም ምልክት ስለማያሳዩ, የመጀመሪያ ደረጃ መከላከያ መንገዶች (ማለትም, ክትባት) እና ሁለተኛ ደረጃ መከላከል መንገዶች (ማለትም, ቅድመ ካንሰር ምርመራ) አስፈላጊ ናቸው። 

በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ በሴቶች ላይ ከተለመዱ ካንሰሮች አንዱ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ መከላከል ይቻላል። የፓፕ ስሚር እና/ወይም የ HPV ዲኤንኤ ምርመራን ያካተቱ የማኅጸን በር ካንሰር ምርመራዎች የካንሰር ቅድመ ሁኔታዎችን እና መጀመሪያ ደረጃ የማህፀን በር ካንሰርን ለመለየት ያገለግላሉ, በየጊዜውም ይከናወናሉ።

ቅድመ ካንሰር ምልክት ታሪክ የሌላቸው እና የበሽታ መቋቋም አቅም ላላቸው ሴቶች፣ እንደ ሴቷ ዕድሜ ላይ በመመስረት ሦስት የምርመራ መንገዶኝ አሉ። 

 • የ HPV ምርመራ ከ21-65 አመት ለሆኑ ሴቶች በየ 5 ዓመቱ ይመከራል።
 • ይህ አይነት ምርመራ ከሌለ ከ30-65 አመት ውስጥ ያሉ ሴቶች በየ 5 አመቱ የጋራ ምርመራ (የHPV ምርመራ ከፓፕ ስሚር ጋር ተጣምረው) ወይም፣
 • ከ21-65 እድሜ በየ 3 አመቱ የፓፕ ስሚር ምርመራ ማድረግ ይመከራ። 

ውጤቱ የቅድመ ካንሰር ምልክት ካላሳየ በተገቢው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ክትትሉን ይቀጥሉ የቅድመ ካንሰር ምልክት ከተገኘ ግን ተጨማሪ ምርመራው ያስፈልጋል ክትትሉም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል።

ማስታወስ ያለብዎት አስፈላጊ ነገሮች:

  • እድሜው ከ 65 ዓመት በላይ ከሆነ እና የቀደሙት ምርመራዎች ሁሉም ቅድመ ካንሰር ምልክት ካላሳየ ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልግም::
  • የበሽታ ተጋላጭነት ካለ (የበሽታ የመቋቋም ሁኔታ መቀነስ ወይም ኤችአይቪ ፖዘቲቭ) ነገር ግን አማካይ የህይወት ዘመን ካለ፣ ከላይ በተገለጸው ፕሮቶኮል መሰረት ምርመራውን ይቀጥሉ።
 • ይህ የቅድመ ካንሰር ምርመራ የHIV ታማሚዎች ከሆኑ ግንኙነት በጀመሩ ጊዜ ጀምሮ ቅድመ ካንሰር ምርመራውን ማከናወን ይኖርባቸዋል (21 አመት መጠበቅ አይኖርባቸውም) እና የፓፕ ስሚር የኤችአይቪ ምርመራ ከተደረገ በኋላ በአንደኛው አመት ሁለት ጊዜ መደረግ አለበት ከዛ ዓመታዊ ክትትል ያስፈልጋል።

አስተያየት ይስጡ

 1. ጄሪ ኤል ግንቦት 15, 2023 በ8:06 ፒኤም - መልስ

  በጣም ጠቃሚ አመሰግናለሁ!

ተዛማጅ ልጥፎች