የቅድመ ወሊድ ደም መፍሰስ

በእርግዝና ጊዜ የደም መፍሰስ በየትኛዉም ወር ሊያጋጥም ይችላል።የቅድመ ወሊድ ደም መፍሰስ(APH) ከ28 ሳምንት እርግዝና በሁዋላ የሚከሰት ደም መፍሰስ ነው። የቅድመ ወሊድ ደም መፍሰስ (APH) ከ 3-5 % የሚሆኑ እርግዝናዎች ላይ ይከሰታል።

የተለያዩ መንስኤዎች የቅድመ ወሊድ ደም መፍሰስ ሊያመጡ ይችላሉ። ከነሱም ዉስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት ሁለቱ ኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ እና የእንግዴ ፕሪቪያ ይገኙንበታል።

ኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ

ኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ ወይም የእንግዴ ልጅ መላቀቅ ሕፃኑን ከመውለዱ በፊት በተለምዶ የተተከለው የእንግዴ ልጅ ከማህፀን ግድግዳ ያለጊዜው መለየትን ያመለክታል። ይህ ከ 100 እርግዝና በ 1 ውስጥ ይከሰታል።

ለዚህ ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል፥ 

  • የእናቶች ዕድሜ መጨመር እና የወሊድ ቁጥር መጨመር፣ የእናቶች እጽ መጠቀም (ሲጋራ ​​ማጨስ, ኮኬይን አላግባብ መጠቀም)፣ ጉዳት (መውደቅ፣ መመታት ወይም የሞተር ተሽከርካሪ አደጋ) ፣የእናቶች ተጉዋዳኝ በሽታዎች (ከፍተኛ የደም ግፊት, ሃይፖታይሮዲዝም, አስም)፣ የእንሽርት ውሃ ከወሊድ በፊት መፍሰስ፣ በእርግዝና ጊዜ ተወጥሮ የነበረው ማህጸን ከወሊድ በሁአላ በፍጥነት ወደ ቀድሞ መጠኑ ሲመለስ ወይም ሲኮማተር ለምሳሌ የመንታ እርግዝና ወሊድ ጊዜ፣ የማሕፀን እና የእንግዴ መንስኤዎች (የማህጸን አፈጣጠር ችግር፣ የመውለድ ኦፕሬሽን ጠባሳ፣ ያልተለመደ የእንግዴ ምስረታ) ሊጠቀሱ ይችላሉ
  • የእንሽርት ውሃ ከወሊድ በፊት መፍሰስ፣ በእርግዝና ጊዜ ተወጥሮ የነበረው ማህጸን ከወሊድ በሁአላ በፍጥነት ወደ ቀድሞ መጠኑ ሲመለስ ወይም ሲኮማተር ለምሳሌ የመንታ እርግዝና ወሊድ ጊዜ፣ የማሕፀን እና የእንግዴ መንስኤዎች (የማህጸን አፈጣጠር ችግር፣ የመውለድ ኦፕሬሽን ጠባሳ፣ ያልተለመደ የእንግዴ ምስረታ) ሊጠቀሱ ይችላሉ
  •  ከዚህ በፊት ኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ የነበራት እናት በቀጣይ እርግዝና ላይ ከ5-15 በመቶ በድጋሚ የመከሰት እድል ሲኖረው ሁለት ተከታታይ ኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ ከነበረ ወደ 25በመቶይጨምራል።

ምልክቶቹ : ከማህጸን ደም መፍሰስ, የሆድ ህመም, የማህፀን መወጠር ሲሆኑ ምልክቶቹን ካዩ ኣቅራቢያዎ ወዳለ ህክምና በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ኣስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የእንግዴ መላቀቅ ከቀጠለ የጽንስ መታፈን እንዲሁም የፅንስ ሞት ሊከሰት ይችላል። ከ10-20% የሚሆነው የኣብረፕሽኦ ፕላሴንታ ደም መፍሰስ የተደበቀ ሊሆን ስለሚችል የፈሰሰው ደም ከሁኔታው ከባድነት ጋር ኣይምዱ። 

 

ፕላሴንታ ፕሪቪያ

   ፕላሴንታ ፕረቪያ በማህጸን ወስጥ ትክክለኛ ያልሆነ የእንግዴ ኣቀማመጥ ሲሆን ይህም እንግዴው ከማህፀን በር ጫፍ ወይም ከጎን ሲቀመጥ ነው። ይህም ከ200 ከሚወለዱ ህጻናት 1 ውስጥ ይከሰታል።

ትክክልኛ ያልሆነ የእንግዴ አቀማመጥ ሁለት አይነት ሊሆን ይችላል የመጀመሪያው ትሩ ፕላሴንታ ፕሪቪያ (True Placenta) ሲሆን ይህም እንግዴው የማኅጸን ጫፍን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ሲሆን እና ሎው ላይንግ ፕላሴንታዴ ፕሪቪያ(low lying) ደግሞ እንግዴው ከማህፀን በር ጫፍ በ2 ሴ.ሜ ርቀት ላይ ሲገኝ ሆኖም ግን አይሸፍነውም።

    ለዚህ ተጋላጭነት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል የእናቶች እድሜ መጨመር፣ የወሊድ ቁጥር መጨመር ፣ የአደገኛ እጽ መጠቀም (እንደ ሲጋራ፣ ኮኬይን መጠቀም)። የጽንሱ ሁኔታዎችም ለዚ የተዛባ የእንግዴ አቀማመጥ አስተዋጽኦ አላቸው ለምሳሌ የመንታ እርግዝና ሲኖር እንዲሁም ወንድ ጽንስ ምክያቱም ወንድ ጽንስ ከሴት ጽንስ ቆይቶ በማህጸን ላይ ስለሚያርፍ ነው።

  ከዚህ በፊት የእንግዴ ፕሪቪያ የነበራት እናት ለቀጣይ እርግዝና ተጋላጭነቷ በስምንት እጥፍ ይጨምራል በተጨማሪም የማህፀን ቀዶ ጥገና እና የወሊድ ኦፕሬሽን ጠባሳ ከዚህ ቀደም 1 የወሊድ ኦፕሬሽን ያላት ሴት ከ1-4 በመቶ የእንግዴ ፕሪቪያ የመጋለጥ እድል ይኖራታል።

    ምልክቶቹም ህመም የሌለው ደማቅ ቀይ ደም ከማህጸን መፍሰስ ሲሆን ከላይ ያሉት ምልክቶች ሲታዩ የህክምና እርዳታ መጎብኘት አለብዎት።ትሩ ፕላሴንታ ፕሪቪያ ያላት እናት በኦፕሬሽን ከ36 እስከ 37 ሳምንት መውለድ ሲኖርባት ሎው ላዪንግ ከሆነ በቅርብ ክትትል እና የድንገተኛ ጊዜ ኦፕሬሽን ባላቸው የህክምና ቦታዎች በማህጸን መውለድ ትችላለች። ነገር ግን ደም መፍሰሱ ካልቆመ ወይም የጸንስ መታፈን ካለ የወሊድ ቀን ባይደርስም በኦፕሬሽን እንድትወልድ ይደረጋል።

ለበለጠ የህክምና ይዘቶች ድህረ ገጻችንን ይመልከቱ።ገጻችንን በኢንስታግራም፣ ፌስቡክ፣ ሊንክዲን፣ ትዊተር መከታተል እንዳትረሱ እና ስለእንደዚህ አይነት ጉዳዮች የበለጠ ለማወቅ የቴሌግራም ማህበረሰብ ቡድናችንን ይቀላቀሉ።

ዶ/ር ብሌን ተስፉ