ምድቦች: Maternal and Nursing
አጋራ

መውለድን ለመጨመር የተለያዩ ምግቦችን ሞክረው ያውቃሉ? ማርገዝ አለመቻል ልብን የሚሰብር እና የሚያስጨንቅ ነገር ሊሆን ይችላል። 

12 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለማርገዝ ይቸገራሉ። ነገር ግን እንደ ቸኮሌት እና ጎጂ ቤሪ ወይም ሌላ ማንኛውንም ነገር መመገብ ለመፀነስ አይረዳዎትም። የማርገዝ እድል ለመሻሻልን ከተለመደው ጤናማ ምግብ ውጩ ልዩ የሆኑ የአመጋገብ ለውጦችን ማረግ አይመክርም። 

ይሁን እንጂ ከመጠን በላይ መወፈር ከወሊድ መቀነስ ጋር ተያያዥ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የልጅነት ውፍረት ከወር አበባ መዛባት እና መካንነት ጋር የተያያዘ ነው። የክብደት መቀነስ ወደ ተሻለ አጠቃላይ ጤና ከመምራት በተጨማሪ የተሻለ የመፀነስ እድሎችን እንደሚጨምር እና ለእርግዝና ህክምናን የመፈለግ እድሎችን እንደሚቀንስ ታይቷል።

ለማርገዝ እየሞከሩ ከሆነ፣ ማድረግ ያለብዎት ነገር ለማወቅ የእርስዎን የማጸን ሃኪም (OB/GYN) ማናገር አስፈላጊ ነው። ምርመራዎችን በማረግ መፀነስን ቀላል ለማድረግ መድሃኒት ወይም የሆርሞን ቴራፒ ያስፈልግዎት እንደሆነ ከሃኪሙ ጋር መወሰን ይቻላል።