ምድቦች: Family Planning
አጋራ

ፍጹም የሆነ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ እንዳለ አስበው ያውቃሉ? ለሁሉም የሚስማማ የወሊድ መከላከያ አይነት የለም። ይልቁንስ ለእርስዎ ልዩ ግምት ውስጥ የሚገቡ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

ሴቶች በራሳቸው ፍላጎት መሰረት የወሊድ መከላከያ ሊመርጡ ይችላሉ። አንዳንዶች እርግዝናን ለመከላከል በጣም ውጤታማ የሆነውን ይመርጣሉ፣ አንዳንዶቹ ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነውን ይፈልጋሉ። አንዳንዶች ጥቂት ወይም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለበትን ሊመርጡ ይችላሉ። አንዳንዶች ደሞ ሴቷ ዘዴውን መቆጣጠር የማትችልበትን እና ዘዴውን እንደምትጠቀም ማንም ሊያውቅ የማይችልበትን ብቻ ይፈልጉ ይሆናል። በወር አበባ ጊዜያት ምንም ለውጥ የማያመጣውን ዘዴ የሚመርጡ ሴቶችም አሉ።

ሕክምና ማድረጎ እና የወር አበባዎን መቆጣጠር መፈለግ ምክኛት ሊታሰብባቸው የሚገቡ ናቸው። በእርስዎ የአኗኗር ዘይቤ እና ልምዶች ላይ እንዲሁም በባልደረባዎ ምርጫዎች ላይ የተመሰረተም ይሆናል። ስለዚህ ለርስዎ ተስማሚ የሆኑ የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ አማራጮችን ለማወቅ እንዲያነቡ እንዲሁም የጤና ባለሙያን እንዲያማክሩ እንመክራለን።