ምድቦች: Family Planning
አጋራ

ቋሚ የወሊድ መቆጣጠሪያን አስበው ያውቃሉ? ማምከን እርግዝናን ለመከላከል እጅግ በጣም ውጤታማ የሆነ ቋሚ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ነው። ቋሚ የሴት የወሊድ መከላከያ በአለም አቀፍ ደረጃ በጣም ከተለመዱት የእርግዝና መከላከያ ዓይነቶች አንዱ ነው። በወሲባዊ ተግባር፣ በእንቁላል ክምችት ወይም በጡት ካንሰር መከሰት ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ የለውም። ነገር ግን ሃሳብዎን ከቀየሩ ወደ ኋላ መመለስ ከባድ ነው፣ ከአባላዘር በሽታዎችም አይከላከልም። 

በቅድመ ወሊድ የቋሚ የወሊድ መከላከያ ፍላጎትን የሚገልጹ እርጉዝ እናቶች ወዲያውኑ ከወሊድ በኋላ ቋሚ የወሊድ መከላከያ ማግኘት ይችላሉ። በድህረ ወሊድ ጊዜ ያለው አሰራር ብዙውን ጊዜ አስተማማኝ እና ምቹ ነው።

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ማምከን ይችላሉ። ለሴቶች የቱቦ ቧንቧ ይታሠራል፤ ለወንዶች ደሞ ቫዜክቶሚ (Vasectomy) ይሰራላቸዋል። ከመስማማትዎ በፊት በቂ ማማከር እና ስምምነት ግን ያስፈልጋል።