አጋራ

ለአባላዘር በሽታ ክትባት ወስደው ያውቃሉ? ውጤታማ የሆነ ክትባት በመጠቀም ሊከላከሉ የሚችሉ አንዳንድ ተላላፊ በሽታዎች አሉ።

እነዚህም HPV፣ ሄፓታይተስ ቢ (Hepatitis B) እና አልፎ አልፎ ሄፓታይተስ ኤ ቫይረስ (Hepatitis A) ያካትታሉ። መከተብ ከባድ በሽታን ይከላከላል እንዲሁም ለችግሮቹ ቅድመ ሁኔታን ይቀንሳል። እንዲሁም ለሌላ ሰው የሚያስተላልፍ ተሸካሚ የመሆን እድሎችን ይቀንሳል።

በአሁኑ ጊዜ HPV፣ Hepatitis A እና Hepatitis B በክትባት ሊከላከሉ የሚችሉ ሦስቱ የአባላዘር በሽታዎች ናቸው። Hepatitis B እና የ HPV ክትባቶች በኢትዮጵያ ይገኛሉ። 

ከክትባቶች የሚለየው የድህረ ተጋላጭነት ፕሮፊላክሲስ በመባል የሚታወቅ ነገር አለ። ይህም ማለት ለበሽታው ከተጋለጡ በኋላ የሚሰጥ ክትባት ሲሆን በሰውነታቸው በሽታው ለረጅም ጊዜ ሳይቆይ በፊት የመከላከል አቅምን ይሰጣሉ። እንደ ኤች አይ ቪ (HIV) ባሉ ጉዳዮች ላይ ደሞ አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተያዘው ሰው ጋር ግንኙነት ባደረገበት ጊዜ ከተጋለጡ በኋላ የመከላከያ መድሐኒት ሊሰጥ ይችላል።

ሌሎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ጨብጥ፣ ክላሚዲያ እና ቂጥኝ ጨምሮ፣ እስካሁን የመከላከያ ክትባት የላቸውም።