ይህን ያውቁ ኖሯል? ዝቅተኛ በራስ የመተማመን ስሜት፣ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እና አካላዊ ድካም የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል። የመንፈስ ጭንቀት ወደ Anorgasmia (ወይም ኦርጋዝም የማረግ ችግር) እና ለወንድ የብልት መቆም ችግር ሊያስከትል ይችላል።
ለድብርት የሚወሰዱ መድኃኒቶች የመንፈስ ጭንቀትን በማቃለል ረገድ በጣም ውጤታማ ናቸው። ነገር ግን ብዙዎቹ እነዚህ መድሃኒቶች ከጾታዊ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር ይመጣሉ።
ድካም እና ውጥረት ለዝቅተኛ ፍላጎት እና ለወሲብ ችግሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ሥር የሰደደ የእንቅልፍ ችግርን ማከም፣ የሥራ ሰዓትን ማስተካከል፣ እና በሕጻናት እንክብካቤ እና በቤተሰብ ኃላፊነቶች ላይ እገዛ ማድረግ ብዙውን ጊዜ በጋብቻ ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያሻሽላል። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በሌሎች የመዝናኛ ዘዴዎች ውጥረትን መቀነስ የተሻሻለ የጾታ ፍላጎት እና እርካታን ያስገኛል።
ሰውነትዎን ሙሉ በሙሉ መረዳት እንዲችሉ ስለ ስነ ተዋልዶ ጤና የበለጠ እንዲያነቡ እንመክርዎታለን።
Medical Information Disclaimer
This information and content is not designed to and does not provide medical advice, professional diagnosis, opinion, treatment, or services to you or to any other individual. It is for providing general information for educational purposes only and is not a substitute for medical or professional care.
Sources:
[1] UpToDate