ምድቦች: Family Planning
አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? የመፈጠር እድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም ጡት በሚያጠቡበት ወቅት ማርገዝ ይችላሉ። ጡት ማጥባት ለእርግዝና የሚዘጋጀውን እንቁላልን መለቀቅ (ovulation) የሚገታ የሆርሞን መጠን ይጨምራል። ስለዚህ እናቶች የወር አበባቸው ባለመኖሩ ብቻ ማርገዝ እንደማይችሉ ያስባሉ።

Ovulation ሊከሰት ቢችልም እራሱ ይህ ተፈጥሯዊ የወሊድ መከላከያ ዘዴ እርግዝናን ስለሚከላከላል በብዙ ሴቶች ይመረጣል። ቢሆንም ግን የወር አበባ ባይኖርም እራሱ እርግዝና ሊፈጠር እንደሚችል በደንብ ማወቅ አለባቸው። እናቶች ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ካሰቡ የወሊድ መከላከያ መጠቀም አለባቸው።

የእርግዝና መከላከያ ምርጫ ቀድሞ በእርግዝና ወቅት ማሰብ አስፈላጊ ነው። አንዱን ከመወሰንዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መማከር ያስፈልጋል። ምን ዓይነት የወሊድ መከላከያ የተሻለ እንደሆነ ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ።