አንዳንድ የአባላዘር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ምልክት የላቸውም። አንድ ሰው የሕመም ምልክቶች ስላላደረበት የአባላዘር በሽታ የለውም ማለት እንዳልሆነ ማወቅዎን ያረጋግጡ።
በአንዳንድ ሁኔታዎች ተላላፊው ረቂቅ ተሕዋስያን እንደ ሄርፒስ (Herpes) በነርቭ ውስጥ ተኝተው ሊቆዩ ይችላሉ። እንደ ቂጥኝ (Syphilis) ባሉት ጊዜ ደሞ ከአንድ የኢንፌክሽን ደረጃ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመሸጋገር ጊዜ ይወስዳል እና ይህ በሽታ የጠፋ ሊመስል ይችላል። እንደ HPV ወይም HIV ባሉ ሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ኢንፌክሽኑ የመጨረሻ በሽታ መልኩ ለመታየት ዓመታት ሊወስድ ይችላል።
ለምሳሌ፣ 70% የሚሆኑ ሴቶች እና 50% የሚሆኑት ክላሚዲያ ያለባቸው ወንዶች ግልጽ ምልክቶች ባይኖራቸውም አሁንም ኢንፌክሽኑን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ከበሽታው በኋላ ባሉት 1 - 2 ሳምንታት ውስጥ ምልክቶች ሊታዩ ቢችሉም አንዳንዴ ከሳምንታት እስከ ወራቶች እንዲሁም ለአንድ አመትም ቢሆን ምንም ምልክት ሊያሳይዎት ይችላል። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ እንደ ኮንኖም አይነት እራስን መጠበቂያ መጠቀምዎን እንዲያረጋግጡ እንመክርዎታለን።
Medical Information Disclaimer
This information and content is not designed to and does not provide medical advice, professional diagnosis, opinion, treatment, or services to you or to any other individual. It is for providing general information for educational purposes only and is not a substitute for medical or professional care.
Sources: