ምድቦች: Family Planning
አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? በማህፀን ውስጥ የሚቀመጡ የእርግዝና መከላከያ መሳሪያዎች (IUDs) ከ 99% በላይ ውጤታማ ናቸው። በማህፀን ውስጥ ያለ መሳሪያ ዶክተርዎ በማህፀን ውስጥ የሚያስገባ (T) ቅርጽ ያለው ነገር ነው። በመዳብ ወይም በሆርሞን ላይ የተመሠረተ ይፈልጉ እንደሆነ ይመርጣሉ።

እርግዝና የሚከለከለው በ IUD እራሱ ባለው ፍሬም በሚፈጠር የውጭ አካል ተጽእኖ እና በሚለቀቀው ሆርሞን መድሃኒት በሚከሰቱ የአካባቢ ለውጦች ነው።

በመዳብ ላይ የተመሰረተው IUD ለ10 አመታት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። በሆርሞን ላይ የተመሰረተው ግን ከ3 እስከ 5 ዓመታት ሊደርስ ይችላል። ምንም አይነት እርምጃ የማይፈልግ የወሊድ መከላከያ መሆኑ ከውጤታማነቱ በተጨማሪ ተመራጭ ያደርገዋል። ለድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንደ አማራጭ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ለቀጣይ አገልግሎትም እዚያው ይቀመጣል። በአጠቃላይ በስፋት ከሚመረጡት የወሊድ መከላከያ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ብዙ ጥቅሞች ስላሉት ነው።