አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? ማንኛውንም የወሲብ ድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ሙሉ ፍቃድ መጠየቅ እና መነጋገር አለብን። የወሲብ ስምምነት በወሲባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ የሚደረግ ስምምነት ነው። ከአንድ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸምዎ በፊት ከእርስዎ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይፈልጉ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልግዎታል። እንዲሁም ስለምትፈልጉት እና ስለማትፈልጉት ድችጊቶች ለባልደረባዎ ሐቀኛ መሆን አስፈላጊ ነው። ይህ ማንኛውም ሰው መብቱ እንደተከበረ እንዲሰማው ለማድረግ ይጠቅማል።

ማስጠንቀቂያ፡ ያለፈቃድ ወሲባዊ ግንኙነት (ምንም አይነት ሌሎች የወሲብ ድርጊቶችንም ጨምሮ) ማረግ ማለት ወሲባዊ ጥቃት ወይም መደፈር ነው። ስምምነት እና ፈቃድ መጠየቅ ማለት የግል መብቶችን ማክበር፣ አጋርዎን ማክበር እና ነገሮች ግልጽ ካልሆኑ ማረጋገጥ ናቸው። ሁለቱም ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት መስማማት አለባቸው እና በእያንዳንዱ ጊዜም ስምምነት ላይ ለመድረስ ያስፈልጋል።