አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ወሲባዊ ድርጊቶች ካንሰርን የሚያስከትል ተህዋሲያን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎችን ሊያሰራጭ ይችላል።

በወሲብ ጊዜ የአፍ እና የፊንጢጣ ንክኪ እንዲሁም ሌሎች ወሲባዊ ድርጊቶች የሚያረጉ ሰዎችን ከሄርፒስ (Herpes) በተጨማሪ ለብዙ የአባላዘር በሽታዎች ያጋልጣሉ። ክላሚዲያ፣ ቂጥኝ እና ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ከነዚህ መሃል የሚጠቀኑ ናቸው።

የሴት እና የወንድ የውጭ ብልት አካባቢ ንክኪ እንኳን እራሱ ከHPV ስርጭት ጋር የተገናኘ ነው፡ ለዚህም ኮንዶም የHPV ኢንፌክሽንን እና የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል 100% ውጤታማ ላይሆን ይችላል። እና ብዙውን ጊዜ ከካንሰር ጋር የተያያዘው HPV ነው።

ሰውነትዎን ሙሉ በሙሉ መረዳት እንዲችሉ ስለ ስነ ተዋልዶ ጤና የበለጠ እንዲያነቡ እንመክርዎታለን።