ምድቦች: Family Planning
አጋራ

የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ሲወስዱ ሌላ መድሃኒት አብረው ወስደዋል?

የኢንፌክሽን መድሃኒት (antibiotics) እና የሚጥል በሽታ መድሃኒቶችን (anti-seizure) ጨምሮ አንዳንድ መድሃኒቶች የወሊድ መከላከያ ክኒኖችን ውጤታማነት ይቀንሳሉ።.

አንዳንድ መድሃኒቶች የሆርሞን የወሊድ መከላከያ ወደ ሰውነትዎ ከገባ በኋላ እንቅስቃሴን ይለውጣሉ። አንዳንድ ከዕፅዋት የተቀመሙ እና አንዳንድ ኤችአይቪን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶች የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ምን ያህል እንደሚሠሩ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

የማህፀን ውስጥ ያሉ እና በቆዳ ዊስጥ የሚቀመጡ የወሊድ መከላከያ መሳሪያዎች ላይ ደሞ ተጽኖ ላይኖር ይችላል።

ያለሀኪም የሚገዙ ክኒኖች፣ ከእፅዋት የተቀመሙ እና የመዝናኛ መድሃኒቶች ይሚወስዱ ከሆነ ሁሉም ለሀኪምዎ ይንገሩ። ሀኪሙ ሊመጡ የሚችሉ ችግሮችን ይነግሮታል። መድሃኒቱን ጨርሰው ወደ ድሮ ጤንነት እስኪመለሱ ድረስ እንደ ኮንዶም ያሉ ተጨማሪ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ሊኖርብዎ ይችላል።