ምድቦች: Products
አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? ታምፖኖች እና ፓድ የእርስዎ ብቸኛ ምርጫዎች አይደሉም። የወር አበባ ሲመጣ የሚያግዞት ተጨማሪ አማራጮች አሉ። 

የወር አበባ ካፕ ከብልትዎ ውስጥ የሚገባ እና በወር አበባ ጊዜ ደም የሚሰበስብ ተጣጣፊ ካፕ ነው። ሌሎች አማራጮች እንደ የወር አበባ ፓንቶች እጅግ በጣም የሚስቡ ናቸው። ቀላል ፈሳሽ ባለበት ቀናት ብቻውን ወይም ከባድ ፈሳሽ ባለ ጊዜ ደሞ ከታምፖን ጋር ሊለብሱት ይችላሉ። ከታጠቡ በኋላ እንደገና ሊጠቀሙባቸውም ይችላሉ። ሌላው አማራጭ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የጨርቅ ሲሆን ተደጋግመው ሊታጠቡ እና ሊለበሱ ይችላሉ።

እንደ የወር አበባ ዲስኮች ያሉ ምርቶችም አሉ። የወር አበባ ካፕ ታምፖን በሚቀመጥበት የሴት ብልት ቦይ ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን የወር አበባ ዲስኮች ደሞ በሴት ብልት ፎርኒክስ ውስጥ ይቀመጣሉ። ይህ በጣም አስፈላጊ ልዩነት ነው ምክንያቱም ይህ አቀማመጥ ማለት የደም ዝውውርን ስለሚከለከሉ በወሲብ ወቅት ዲስኮች ሊለበሱ ይችላሉ።

የተለያዩ አዳዲስ ምርቶች ለሴቶች በወር አበባ ጊዜ በጣም ምቹ ከማረጋቸው አልፎ ምርጫ ይሰጣቸዋል።