ምድቦች: Family Planning
አጋራ

አብዛኛዎቹ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የወሊድ መከላከያ ክኒን ይጠቀማሉ። ነገር ግን ብዙ ሴቶች የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ለተለያዩ የሴቶች ችግሮችን ለማከም እና አንዳንድ አስገራሚ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት አያውቁም። የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖች የተሰሩት ከተዋሃዱ ከላቦራቶሪ የተገኙ የሁለቱ ሆርሞኖች (ፕሮጄስትሮን እና ኤስትራዶል) አንድ ላይ ወይም ከፕሮጄስትሮን ብቻ ነው። እነዚህ ሆርሞኖች የወር አበባን በመቆጣጠር ረገድ፣ መደበኛ ያልሆነ እና የሚያሰቃዩ የወር አበባዎችን ለማከም፣ የendometriosis ህክምና (ከማህፀን ውጭ የendometrium ቲሹ እድገት)፣ ብጉር ህክምና፣ ከመጠን በላይ የፀጉር ማደግ እንዲሁም የኦቫሪ እና Endometrial ካንሰር በሽታን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ይታወቃል።