አጋራ

ይህን ያውቁ ኖሯል? የወር አበባ መዛባት ምክንያታቶች ይለያያሉ። አንዳንድ ጊዜ የወር አበባው ለመታየት በጣም ረጅም ጊዜ የሚወስድ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ በጣም በተደጋጋሚ ይመጣል ወይም በጣም ብዙ ይፈስሳል። አቀራረቡ በእሱ ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ምክንያቶች ጋር ይለዋወጣል።

ለወር አበባ መዛባት በጣም ከተለመዱት ምክንያቶች አንዱ ጭንቀት ነው። በሰውነት ላይ የሚፈጠር ማንኛውም አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ጭንቀት የሌሎች ሆርሞኖችን ተፈጥሯዊ ሚዛን ሊያዛባ ይችላል። ይህ ዘግይቶ ወይም ቀድሞ የሚመጣ የወር አበባን ሊያስከትል ይችላል። 

በማርገዝ ከፍተኛ እድል ያለበት እድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ደሞ እንደ እጢ አይነት የማህፀን ውስጥ ቁስሎች ወር አበባ መዛባት ሊያመጡ ይችላሉ። በተጨማሪም በኢንፌክሽን ምክንያት እንዲሁም እንደ ታይሮይድ (thyroid) ባሉ ሌሎች የአካል ክፍሎች ችግሮች ምክንያት ሊሆን ይችላል። እንዲሁም የተወሰኑ መድሃኒቶች እና ወሊድ መቆጣጠሪያ መቀየር ጋር ይያያዛል። 

ስለዚህ የወር አበባ መዛባቱ ከባድ ከሆነ ሐኪም ማማከሩ የተሻለ ነው። እንዲሁም አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነትዎን ለመንከባከብ ጭንቀትን ለመቀነስ ጊዜ ይውሰዱ።