አጋራ

የወር አበባ መደበኛ አለመሆኑ የተለመደ ነው። በተለይም የወር አበባ ከጀመሩ በኋላ ባሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሊያጋጥም ይችላል። ሃሳብ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ህመም የወር አበባ ሳይከሰት እንዲያልፍ ሊያደርጋቸው ይቻላል። ብዙ ክብደት ከጨመሩ ወይም ከቀነሱ ሊከሰት ይችላል.

በአንዳንድ ሁኔታዎች የወር አበባዎች ሙሉ በሙሉ ሊቆምም ይችላል። አንዳንድ ጊዜ በተለመደው ለውጦች ምክንያት ሊሆኑ ስለሚቹ ጭንቀት አያስልግም።. ሌላ ጊዜ ግን አንድ አሳሳቢ ነገር እየተካሄደ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች ሊሆኑ ስልሚችሉ ወደ ሐኪምዎ መሄድ ያስፈልጋል።

በሴት ወር አበባ ዑደት ውስጥ የወር አበባ መዘግየትን የሚያስከትሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። እነዚህ ሁሉ የወር አበባ መቅረት የተለመዱ ምክንያቶች ናቸው። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ::

 • እርግዝና
 • ጡት ማጥባት
 • ማረጥ
 • መንፈሳዊ ውጥረት/ ጭንቀት
 • ውፍረት መቀነስ
 • ወሊድ መቆጣጠሪያ መጀመር
 • የሆርሞን ለውጦች
 • የተለያዩ መድሃኒቶች መውሰድ
 • የክብደት መጨመር
 • ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮላክቲን መኖር
 • (Asherman syndrome) የአሸርማን ሲንድሮም
 • የፒቱታሪ ዕጢዎች