ምድቦች: Family Planning
አጋራ

 • የወሊድ መከላከያ ክኒን መውሰድ መርሳት የእርግዝና መፈጠር ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው። ለወደፊቱ እንዳትረሱ እና እርግዝናን ለመከላከል ሌላ አይነት የእርግዝና መከላከያ እንድትጠቀሙ የኛን መተግበሪያ እንድትጠቀሙ እንጋብዛለን።

  አንድ ኪኒን በ24-48 ውስጥ ባለ ሰአት ከረሱ ወይም ለመውሰድ ከ24 ሰአት ባነሰ ጊዜ ከዘገዩ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት:

  • ዘግይቶ ወይም ያመለጠውን ክኒን በተቻለ ፍጥነት ይውሰዱ።
  • የሚቀሩትን ኪኒኖች በአግባቡ ሰአት መውሰድ 
  • በአስፈላጊው ሰአት (Ovulation) ላይ ከሆነ ሳይወስዱ የቀሩት በአስቸኳይ ድንገተኛ ወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ

  ከሁለት በላይ ኪኒን መውሰድ ከረሱ ደሞ፡

  • በቅርቡ ያልወሰዱትን አንድ ኪኒን ብቻ ይውሰዱ (የቀሩት - የተረሱትን ኪኒኖች ሁሉ ይተው)
  • እሱን ከወሰዱ ከዚህ በኋላ የሚቀጥሉትን ኪኒኖች በነበረው ሰአት መውሰድ ይቀጥሉ
  • ተመልሰው ኪኒን መውሰድ ጀምረው 7 ቀን እስኪሞላዎት ድረስ ወይ ከንኙነት ይቆጠቡ ወይም ለወሊድ መከላከያ ኮንዶም ይጠቀሙ።
 • ይጠንቀቁብዙ ኪኒን ሳይወስዱ ረስተው ግንኙነት ካረጉ የድንገተኛ ወሊድ መከላከያ መጠከም ይኖርቦት ይችላል። (የድንገተኛ ወሊድ መከላከያ ከድንገተኛ ሁኔታ ጥቅም ውጪ መጠቀም አያዘውትሩ።) 

  ስለድንገተኛ ወሊድ መከላከያ አጠቃቀም የበለጠ ለማወቅ ሌሎች የሰራናቸውን ቪድዮ ይመልከቱ 

  የወሊድ መከላከያ ኪኒን መጠቀም በተደጋጋሚ እየረሱ ከሆነ ሌላ መከላከያ መጠቀም ያስቡ።