ምድቦች: Family Planning
አጋራ

የወሊድ መከላከያ ስፖንጅ መጠቀም በወሲብ ወቅት የሴት ብልት መድረቅን ሊያስከትል ይችላል።

እውነታ!በወሊድ መከላከያ ስፖንጅ ላይ ያለው የወንድ የዘር ፈሳሽ በተለያዩ ሴቶች ላይ የተለያየ ተጽእኖ ይኖረዋል። አንዳንድ ሰዎች ስፖንጁ እርጥብ እና የተዘበራረቀ ነው ብለው ያማርራሉ። ሌሎች ደሞ ስፖንጅ የሴት ብልትን እርጥበታማነት በመምጠጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ እርጥበት ይቀንሳል ቢሆንም ግን በውሃ ላይ የተመሰረተ ወይም የሲሊኮን ቅባት መጨመር ሁነታውን በማሻሻል ምቹ እንዲሆኑ ይረዳል ይላሉ።

የእርግዝና መከላከያ ስፖንጅ እና የሚለቀቀው የወንድ የዘር ፍሬ መከላከያ መዳኒት የሚከተሉትን ሊያመጣ ይችላል፡-

  • የሴት ብልት አካባቢ መቆጣት ወይም ደረቅነት
  • የሽንት ቱቦ ወይም የሴት ብልት ኢንፌክሽን
  • የአባላዘር በሽታ የመያዝ እድልን ይጨምራል
  • Toxic shock syndrome

የሚከተሉትn ካደረጉ የጤና ባለሙያ የእርግዝና መከላከያ ስፖንጅ ላይፈቅድሎት ይችላል-

  • ለስፐርሚሳይድ ወይም ለ polyurethane አለርጂክ ከሆኑ
  • የወሊድ መከላከያ ስፖንጅ በሚገባበት የሴት ብልት መዛባት ካሎት
  • ብዙ ጊዜ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከነበሮት
  • Toxic shock syndrome ከነበሮት
  • በቅርቡ ከወለዱ ወይም ፅንስ ከወረደቦት
  • በኤች አይ ቪ የመያዝ እድሎት ከፍተኛ ከሆነ ወይም ኤች አይ ቪ ካለቦት::

ስፖንጁ በብልት ውስጥ እያለ ወደ ቁርጥራጭ ከተከፋፈለ ሁሉም ቁርጥራጮች መወገዳቸውን ለማረጋገጥ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ማስታወሻ! በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ቅድመ ወሊድ መከላከያ አጠቃቅም ዘዴ ላይ ስህተት ከነበረ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ሊያስፈልግ ይችላል።