አጋራ

የወር አበባ ለአብዛኛዎቹ ሴቶች ከ3 እስከ 5 ቀን ይቆያል። ግን አይጨነቁ! አንድ ሴት የወር አበባ ለ2 ቅን ብቻ ወይም እስከ 8 ቀን ድረስ ሊቆይ ይችላል። በተከታታይ ከ7 ቀናት በላይ ደም እየፈሰሰ ከሆነ, ግን ሐኪምዎን ያነጋግሩ::

የወር አበባ ቀን መርዘም ምክንያቶች እንደ የራስ የጤና ሁኔታ፣ እድሜ እና የአኗኗር ዘይቤ ሊሆኑ ይችላል። ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የጤና እክሎች ካንሰር የሆነ (endometrial cancer) ወይም ያልሆነ የማህፀን እጢ (Myoma)፣ endometrial (የማህፀን) ፖሊፕ፣ አዶኖሚዮሲስ፣ ወይም አልፎ አልፎ፣ የቅድመ ካንሰር ወይም የማህፀን ካንሰርን ሊያካትት ይችላል። በተጨማሪ በሆርሞን መዛባት በእንቅርት ችግር (Hypothyroidism) ወይም በደም መፍሰስ አለማቆም ችግር ሊከሰት ይችላል::

ያልተለመዱ የወር አበባ ችግሮች (በቀን ብዙ ሞዲስ ወይም ታምፖን መለወጥ ወይም 5 ሳምንታት በላይ ቆይቶ መምጣት) በጤና ባለሙያ መገምገም አለባቸው። የወር አበባ ዑደት (cycle) ባህሪያት ለውጥ (እንደ የድግግሞሽ፣ የደም መፍሰስ መብዛት እና በወር አበባ መካከል የሚታይ ተጨማር ደም መፍሰስ) የህክምና አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ምክንያት ናቸው።

በአንድ ሕመም ምክንያት ረዥም የወር አበባ መኖር ለማስተካከል የመጀመሪያው እርምጃ ህክምና ነው። ይህ እንደ ማህጸን ላይ ያለ እድገት (endometrial polyp) ማስወገድ ወይም የእንቅርት ሆርሞን መጠን ማነስ (hypothyroidism) ማስተካከል ያሉትን ሊያካትት ይችላል። የሆርሞን የወሊድ መከላከያ (እንደ ክኒን፣ ፓች ወይም ሆርሞን IUD) የሚመጡ ያልተለመዱ ዑደት (cycle) መዛባትን ለመቆጣጠር በተለምዶ ጥቅም ላይ ይውላሉ። መሻሻል ወይም ለውጥ ከማየትዎ በፊት ግን እነዚህ ዘዴዎች በአብዛኛው ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ይፈጃሉ::