አጋራ

ታምፖኖች ወደ ቶክሲክ ሾክ ሲንድረም (TSS) የሚያመሩ ኢንፌክሽኖች ሊያመጡ ይችላሉ። ታምፖኖች ደም ለመምጠጥ ይሰራሉ። ወደ ብልትዎ ውስጥ ካስገቡ በኋላ የወር አበባዎን ደም በመምጠጥ ሲቆይ በሴት ብልትዎ ውስጥ ያሉት ጡንቻዎች በሰውነትዎ ውስጥ እንዳይጠፋ ይይዙታል። አንድ ጊዜ ከገባ መኖሩ ሊሰማዎት አይገባም::

ታምፖን በየ4 - 8 ሰአት እንዲቀይሩ ይመከራል። ለመጠንቀቅ ግን ከ6 ሰአት በላይ አለማቆየት የኢንፌክሽን መፈጠር እድሉን ይቀንሳል። ሲተኙ መጠቀም ከፈለጉ ሲነሱ ወድያው እስከቀየሩት ድረስ ተመራጭ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ነው።

ለወር አበባ ፍሰት የመምጠት ችሎታው ጥሩ የሆነው መምረጥ አስፈላጊ ነው። የወር አበባ ፍሰትዎ ከቀን ወደ ቀን ስለሚለዋወጥ የተለያዩ ቀናት ውስጥ የተለያዩ መምጠጥ ችሎታ ያለውን ታምፖን መጠቀም ይመረጣል። የታምፖን መምጠጥ ችሎታ ለማወቅ መጀመሪያ ላይ ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል። ግን ቀላል ለማረግ እንደዚ ይያዙት - የሚጠቀሙትታምፖን ለመለወጥ የማይመች ከሆነ መጠኑን ይቀንሱ። የሚጠቀሙት ታምፖን የሚያፈስ ከሆነ ደሞ መጠኑን ከፍ ያድርጉ።

ታምፖን አጠቃቀም ማወቅ ከፈለጉ ለማስተማሪያ ያዘጋጀነውን ቪዲዮ ይመልከቱ።