አጋራ

በተለምዶ ቢዙ ሊመስል ይችላል እንጂ የብዙ ሴቶች ወር አበባ ፈሳሽ ከ3-4 ማንኪያ በላይ አያልፊም።

ብዙ የወር አበባ ፈሳሽ ነው ለማለት ከሌላ ጊዜ ያለው ፈሳሽ ጋር ማወዳደር ያስፈልጋል። መንሳኤው ደሞ የማህጸን ላይ ያለ እድገት፣ እጢ ወይም ሌላ ችግር ሊሆን ይችላል። 

በጣም ከመጠን በላይ ከሆነ በአስቸኳይ የጤና ባለሙያ ማናገር ያስፈሊጋል። ብዙ ደም መፍሰስ ሌላ አሳሳቢ ችግሮች (እንደ ያልታሰበ የጽንስ ውርጃ) ሊሆን ይችላል። የሴት አካል ላይ ጉዳት ከደረሰም በዚ ምክኛት ሊሆን ይችላል። በጣም በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ የደም ማነስ ሊያስከትል እና ወደ ድካም እና ማዞር ሊያመራ ይችላል 

በቀን ከ10 በላይ ታምፖን ወይም ፓድ መጠቀም ወይም በየ 1 ሰአት ታምፖን ወይም ፓድ መቀየር ካስፈለገ በአስቸኳይ ሃኪም ማናገር ያስፈልጋል።