ምድቦች: Family Planning
አጋራ

መልሱ አዎ ከሆነ አይደንግጡ። ከ50% በላይ የሚሆኑ ሴቶች የሚወጋ ወሊድ መከላከያ መጠቀም ከጀመሩ በኋላ የወር አበባ መቋረጥ ወይም መቅረት ለ1 አመት ያጋጥማቸዋል። ግን ይሄ ሰውነታችን ውስጥ ያለው ሆርሞን እስከየሚስተካከል ሲለሚቆይ ነው።

Ovary በቀላሉ ለማስረዳት በእረፍት ላይ ናቸው። በየወሩ እንቁላል አይለቀቁም። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሰውነትዎ በየወሩ የወር አበባ ፈሳሽ መፍሰስ አይኖረውም።. የወር አበባም አይኖርም። የ Depo-Provera የወሊድ መከላከያ መርፌን መጠቀም ሲያቆሙ የወር አበባዎ ከሆነ ጊዜ በኋላ ወደ መደበኛው ሁኔታ ይመለሳል።

መርፌውን እስካላዘገዩ ወይም እስካላሳለፉ ድረስ የወር አበባዎ ቢቆምም እርጉዝ ላይሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን እርጉዝ ልሆን እችላለው ብለው ካሰቡ ወዲያውኑ የጤና ባለሙያ ያነጋግሩ።

ልክ እንደ ኪኒን መርፌ ሲጠቀሙ አብረው የሚመጡ ችግሮች አሉ። ያልጊዜ መድማት፣ ራስ ምታት፣ ድካም፣ የጡት ህመም፣ ማዞር፣ የሆድ ህመም፣ ድብርት እና በዋነኝነት ኪሎ መጨመር መጥቀስ ይቻላል። እንደማንኛውም መድሃኒት ከመጀመሮት በፊት የጤና ባለሙያ ማማከር ይመረጣል።