ምድቦች: Family Planning
አጋራ

አንዳንድ የዘር ፍሬ መከላከያ መድሐኒቶች የጾታ ብልትን ማስቆጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህም የአባላዘር በሽታ የመያዝ እድልን ይጨምራል።

እውነታ! ስፐርሚሳይድ (spermicide) መጠቀም ከኢንፌክሽን የሚከላከሉትን ህዋሶች ስለሚያስቆጣ ኢንፌክሽን የመያዝ እድል ሊጨምር ይችላል። ይህ እነዚያን መከላከያ ሴሎች ያዳክማል እና ለባክቴሪያዎች የበለጠ ተጋላጭ ያደርግዎታል። በዚህ ምክንያት በSTD የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ለሆኑ ግለሰቦች ስፐርሚክሳይድ አይመከርም።

የስፐርሚሳይድ (Spermicide) ትልቁ ጉዳቶች የሚከተሉት ናቸው።

 • በትክክል ጥቅም ላይ መዋል አለበት እና በመለያው ላይ ባለው መመሪያ መሰረት መጠቀም ግዴታ ነው።
 • የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸሙ ቁጥር እንደገና መተግበር አለበት።
 • በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች (STIs) አይከላከልም።
 • የሰውነት መቆጣት እና ህመም ሊያስከትል ይችላል::
 • በኤች አይ ቪ የመያዝ እድልን ይጨምራል።
 • የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን (UTIs) መጨመር ጋር ተያያዥነት አለው።

ስፐርሚሳይድ (Spermicide) እየተጠቀሙ ከሆነ እና የሚከተሉት ችግሮች ካጋጠሞት የጤና ባለሙያ ያነጋግሩ።

 • ደስ የማይል ሽታ ያለው የሴት ብልት ፈሳሽ።
 • በሴት ብልት ላይ ሽፍታ ወይም ቁስሎች መኖር::
 • የሚያቃጥል ሽንት
 • ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት
 • የታችኛው የሆድ ህመም.
 • ወሲብ ጊዜ ህመም::