ምድቦች: Family Planning
አጋራ

እውነት ወይስ ሃሰት፡ በወሲብ ወቅት ከአንድ በላይ ኮንዶም መጠቀም በሁለት እጥፍ መከላከያን ይጨምራል።

ሃሰት! በአንድ ጊዜ ሁለት በላቲክስ (Latex) ላይ የተመሰረቱ ምርቶችን መጠቀም ወደ መቀደድ ሊያደርስ ይችህላል። በአንዱ ኮንዶም የሚሰጠው ጥበቃ ይቀንሳል::

የሰውነት ሎሽን፣ እርጥበት ማድረቂያ፣ የመታሻ ዘይት፣ የሰውነት ዘይት፣ ሊፕስቲክ፣ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዘይት ላይ የተመሰረተ ምርት (እንደ ፔትሮሊየም ጄሊ፣ ወይም ቫዝሊን) ከላቲክስ ወይም ከሌላ ነገር የተሰራ ኮንዶም አይጠቀሙ። ኮንዶሙን ሊያዳክሙ ስለሚችል ውጤታማነቱ ይቀንሳል። ብዙ ውሃ ላይ የተመረኮዙ ቅባቶችን እንደ ኬ ዪ ጄሊ (KY Jelly) ለምንም አይነት ወሲብ ድርጊት ይጠቀሙ።

ኮንዶም አስመልክቶ መደረግ ያለባቸው እና የሌለባቸው

 • ያድርጉ ፦ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸሙ ቁጥር ኮንዶም ይጠቀሙ።
 • ያድርጉ ፦ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸምዎ በፊት ኮንዶም ይለብሱ
 • ያድርጉ ፦ ልጣጩን ወይም ካርቶኑን ያንብቡ እና የሚያበቃበትን ቀን ያረጋግጡ
 • ያድርጉ ፦ ቅድ ቦታ አለመኖሩን ያረጋግጡ
 • ያድርጉ ፦ ኮንዶም በቀዝቃዛና ደረቅ ቦታ ውስጥ ያስቀምጡ
 • ያድርጉ ፦ ያድርጉ ፦ የላቲክስ (Latex) ወይም የ polyurethane ኮንዶም ይጠቀሙ
 • ያድርጉ ፦ መድረቅ ለመከላከል በውሃ ላይ የተመሰረተ ወይም በሲሊኮን ላይ የተመሰረተ ቅባት ይጠቀሙ
 • አያድርጉ ፦ ሙቀት ሊጎዳቸው ስለሚችል ኮንዶም በኪስ ቦርሳዎ ውስጥ አያከማቹ።
 • አያድርጉ ፦ ሰውነት መቆጣት ሊፈጥር ስለሚችል nonoxynol-9 (የወንድ የዘር ፈሳሽ መከላከያ መድሐኒት) አይጠቀሙ
 • አያድርጉ ፦ ኮንዶም እንዳይሰራ ስለሚያደርጉ እንደ የህጻን ዘይት፣ ሎሽን፣ ፔትሮሊየም ጄሊ (vaseline) ወይም የምግብ ዘይት የመሳሰሉ ዘይት ላይ የተመሰረቱ ምርቶችን አይጠቀሙ።
 • አያድርጉ ፦ በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ኮንዶም አይጠቀሙ
 • አያድርጉ ፦ ኮንዶም እንደገና በፍጹም አይጠቀሙ::

ማስታወሻ፦የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸሙ ቁጥር ኮንዶም ይጠቀሙ።