አጋራ

ፈቃድ በነጻ መሰጠት አለበት። ፍቃድ መስጠት አደንዛዥ እፅ ወይም አልኮል ሳይወስዱ ያለ ጫና የሚደረግ ምርጫ ነው።

ሊቀየር የሚችል፡ ማንኛውም ሰው ምን ማድረግ እንደማፈልግ በማንኛውም ጊዜ ሀሳቡን መቀየር ይችላል። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ያደርጉት ቢሆንም እንዲሁም አልጋ ላይ ራቁት ድረስ ደርሰው ቢሆንም ሃሳብ መቀየር ይቻላል።

በመረጃ የተደገፈ፡ ለአንድ ነገር መስማማት የሚችሉት ሙሉውን ታሪክ ካሎት ብቻ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ኮንዶም እጠቀማለሁ ብሎ ካልተጠቀመ ሙሉ ስምምነት የለም።

ቀናተኛ፡ ከወሲብ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ማድረግ የሚፈሊጉትን ነገሮች ብቻ እንጂ ማድረግ የሚጠበቅብን የመሰለንን ማረግ አያስፈልግም።

የተወሰነ፡ ለአንድ ነገር አዎ ማለት ነው (እንደ ለመሳሳም ወደ መኝታ ቤት መሄድ) ማለት ለሌሎች ድርጊቶች (እንደ ወሲብ መፈጸም) አዎ ብለዋል ማለት አይደለም።