YeneHealth About Us

ስለ እኛ

ዬኔሄልዝ በመላው አፍሪካ ለሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሴቶች የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ዲጂታል በር እየከፈተ ነው።

ዬኔሄልዝ በሃገር ውስጥ ፣ አፍሪካዊ የተመሰረተ፣ በሴቶች የተመሰረተ እና የሚመራ ድርጅት ሲሆን ዋና መስሪያ ቤታችን አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነው። ስልጣንን በአፍሪካ ሴቶች እጅ ለመመለስ ስንሰራ በዚህ ጉዞ ላይ ይቀላቀሉን!
ዬኔሄልዝ በኢትዮጵያ ላይ የተመሰረተ የመጀመሪያ እርምጃ ላይ ያለ ፌምቴክ ድርጅት ነው። የመጀመሪያውን ለአካባቢያዊ እና ለባህለዊ አመለካከት አስተሳስቦ የተሰራ የወር አበባ-ክትትል እና አጠቃላይ የወሲብ እና የስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት ለአፍሪካዊ ሴቶች የሚሰጥ ዲጂታል መድረክ ገንብተናል።
ለተጠቃሚዎቻችን የመማሪያ ፖርታልን፣ ሴቶችን ያማከለ ኢ-ፋርማሲ እና የቴሌሜድ አገልግሎት ከስልካቸው ግላዊነት እና ምቾት ለማቅረብ ቴክኖሎጂን እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሃይልን እንጠቀማለን።

ዬኔሄልዝ ያዘጋጀው ድር እና የሞባይል መተግበሪያ ብዙ ቋንቋ የያዘ ነው። ለተጠቃሚዎች ልዩ ልምድ ከተለያዩ እርዳታ እና የድጋፍ ባህሪያት ጋር ለግል ተመቻችተው የተበጁ ተሞክሮዎችን ይፈቅዳል። የዬኔሄልዝ መድረክ ላይ መመዝገብ ነፃ፣ ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ተጠቃሚዎች ጤናማ እና አርኪ የሆኑ መተዳደሪያዎችን በልዩ ቅናሽ እንዲሁም የጤና አስተዳደር መሳሪያዎችን እና በዶክተር የሚደገፍ የታመነ መረጃ የማግኘት ዕድል አላቸው።
አገልግሎታችን የጤና መረጃን እና የምርቶች ተደራሽነት በመጨመር እና የሴቶች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በመጠበቅ ረገድ ንቁ እንዲሆኑ በማበረታታት የሴቶች ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ሁሉም የእኛ አቅርቦቶች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ያልተሟሉ የቤተሰብ ምጣኔ እና የእናቶች ጤና ፍላጎቶች ትልቅ ፈተናን ይፈታሉ።
መጨረሻ ላይ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ያሉ ልጃገረዶች እና በመውለድ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶች ርህራሄ እና መገለል በሌለው፣ ሚስጥራዊ እና እራስን ማስተዳደር በሚያስችሉ መሳሪያዎች፣ ግብዓቶች እና የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶች አማካኝነት በአካላቸው ላይ እራሳቸው መወሰን እንዲችሉ እንደግፋለን።

ሴቶች የሚገባቸው እንክብካቤ

በቴክኖሎጂ የታገዘ የወር አበባ፤ የእግዝና እና የመድሃኒት መከታተያ AI powered menstrual, pregnancy, medicine tracker

የሴቶች ማዕከል ኢ-ፋርማሲ ከትእዛዝ ጋር ማቅረቢያ አዘጋጅቶ ወዳሉበት ያደርሳል women-centered e-pharmacy with discreet ordering and delivery/pickup

የተለያዩ ቋንቋ እና ባህላዊ ሚንጭ ያላችው ትምህችታዊ ይዘቶች multilingual and culturally-responsive resources & educational content

ቴሌ ፟ሜዲሰን እና በፈለጉበት ሰአት ነርስ ለማግኘት መደወያ ስልክ Telemed and on-demand nurse call line

Stats screen

የኛ ደጋፊዎች፤ አጋሮች፤ ተባባሪዎች እና ባለሃብቶች